የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ወደ አዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ለሚጓዙ የበዓሉ ተሳታፊች የትራንስፖርት እጥረት እንዳያጋጥም በቂ ዝግጅት ተደርጓል፡፡
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎትና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ጋር ቅንጅት በመፍጠር የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ወደ አዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ለሚጓዙ የበዓሉ ተሳታፊዎች የትራንስፖርት እጥረት እንዳያጋጥም በቂ ዝግጅት ተደርጓል፡፡
ለበዓሉ ተሳታፊዎች የትራንስፖርት እጥረት እንዳያጋጥምና ለሌላውም የትራንስፖርት ተጠቃሚ ማሀበረሰብ ፍትሐዊ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን በዓሉን ለማክበር ወደ አዲስ አበባና ቢሾፍቱ ለሚጓዙ ታዳሚዎች ትራንስፖርት ለማቅረብ ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ በሰጡት አቅጣጫ ኮሚቴ ተማቋቋቂሞ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል፡፡
በዚሀም በአዲስ አበባ በአምስቱም መግቢያ በሮች ወደ በዓሉ ማክበሪያ ቦታ የሚያደርሱ ከአዲስ አበባ ሲቲ ባስ 907 ከተማ አውቶብሶች፣ 400 የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አውቶብሶች ተዘጋጅተዋል፡፡ በተጨማሪም ቢሸፍቱ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል 150 የሚሆኑ አቋራጭና መለስተኛ አውቶቢሶች ዝግጁ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በአጠቃላይ ታክሲዎችን ሳይጨምር 1ሺ 457 ተሽከርካሪዎች ተዘጋጅተዋል፡፡
ለኢሬቻ በዓል ትራንስፖርት አቅርቦት እንዲኖር ሲሰራ መደበኛው የትራንስፖርት ፍሰት እንዳይሰተጓጎልና ፍትሃዊ የሆነ አገልግሎት ማቅረብ እንዲቻል ከፍተኛ ጥንቃቄም ተደርገዋል።
ከባለፉት አመታት ልምድ በመውሰድ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከርና ቀደም ብሎ በመዘጋጀት በዓሉን ያለ ምንም እንግልትና ወከባ እንዲከበር የተሻለ ዝግጅት ማድረግ ተችሏል፡፡
ሁሉም ተሽከርካሪዎች በተለመደው የትራንስፖርት ታሪፍ ብቻ አገልግሎት መስጠት የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህም እንዳይከሰት ክትትል የሚደረግ ይሆናል፡፡
የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች የበዓሉ ተሳታፊዎችን በትህትና፣ በኢትጵያዊነት መስተንግዶ በማገልገል በዓሉን እንደ መልካም አጋጣሚ መጠቀም እንደሚኖርባቸው እናሳስባለን።
በትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ አካባቢዎች ሊስተዋሉ የሚችሉ የጸጥታ ችግሮችን ለማስቀረት ከፀጥታና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰራ ስለሆነ የበዓሉ ተሳታፊዎች ለሚሰጠው የማስተባበርም ሆነ ፀጥታ የማስከበር ስራዎች ተባባሪ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

4 comments
መልካም በዓል ይሁንላቹ
ኦሮሞ የመሆን ጥቅማጥቅም😂
ባይከበርስ ቆይ
ፕሌን አይሻልም ነበር 😌