0
#FastMereja
የእሥራኤል የምድር ጦር ጥቃት በበረታባት ሊባኖስ በቤት ሠራተኝነት የሚያገለግሉ አብዛኞቹ፦ ከኢትዮጵያ፤ ኬንያ፤ ሱዳን፤ እና ሲሪላንካ የሄዱ ሠራተኞች በቀጣሪዎቻቸው ቤት ተዘግቶባቸዋል ተባለ ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደዘገበው ከሆነ፦ አብዛኞቹ ሴቶች የቤት ሠራተኞች ቁጥራቸው ወደ 170,000 ይጠጋል ። ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) አብዛኞቹ የቤት ሠራተኞችን ቀጣሪዎቻቸው ቤት ውስጥ ትተዋቸው እንደሄዱ የሚጠቁሙ አሳሳቢ መረጃዎች እየደረሳቸው መሆኑን ገልጧል ።
የዓለም አቀፉ ድርጅት የሊባኖስ ኃላፊ ማቲው ሉቺያኖ፦ የቤት ሠራተኞቹ ሊባኖሳውያን አሠሪዎቻቸው ሲሸሹ «አንድም ቤት ውስጥ አለያም ጎዳና ላይ ትተዋቸዋል» ሲል የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP) ዘግቧል ።
ካለፈው ማክሰኞ አንስቶ የእሥራኤል ጦር በምድር ሊባኖስ ውስጥ ጥቃት የከፈተ ሲሆን፤ በአየርም ጥቃቱን ማጠናከሩ ተገልጧል ሲል ዶቼ ቬለ ነው የዘገበው።

2 comments
አንጀት ይበላል
ይሄ እነሱን ከዛ ሀገር ላለማሶጣት የጠነሰሰ ሴራ ነው ሚሆነው