banner

በ”ሰናይፐር ይጠበጠባል” መቋጫውን አገኘ! እርቅ ወረደ!

በይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)
#FastMereja

ትናንት በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ሊካሄድ የነበረውና ከኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ አባገዳዎች ሳይመቻቸው በመቅረቱ ያልተከናወነው የጀግኖቹ አትሌቶች ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉና የጀግናው አትሌት ገዛኸኝ አበራ ሽምግልና ዛሬ በዕርቅ ተቋጭቷል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዋናና ምክትል ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት ከጓደኝነትም በላይ ቤተሰቦች የሆኑት ደራርቱና ገዛኸኝ አበራ ቂም ይዘን፣ተኮራርፈን ትልቁን የኦሮሞ ባህል የሆነውን ኢሬቻን አናከብርም፤የእስከአሁኑ ይበቃናል በማለት በዛሬው ዕለት በበዓሉ ዋዜማ እርቀ ሠላም አውርደዋል።

በረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉና በአትሌት ገዛኸኝ አበራ መካከል ተፈጥሮ የነበረው የፀብ ግድግዳ ፈረሠ

ከጥቂት ደቂቃ በፊት በኃይሌ ግራንድ ሆቴል በተካሄደ የእርቅ ስነ-ስርዓት በሁለቱ ጀግኖች አትሌቶች ደራርቱ ቱሉና ገዛኸኝ አበራ መካከል እርቀ ሠላም ወርዷል

ዕርቁ የተሳካ እንዲሆን የቀድሞው አትሌት ወርቁ ቢቂላና ሌላኛው ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ትልቁን ሚና ተጫውተዋል

በዕርቁ ስነ-ስርዓት ላይ አባ ገዳዎች፣ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ፣አትሌት ወርቁ ቢቂላ፣ረዳት ኮሚሽነር ሁሴን ሸቦ፣አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ እና አሠልጣኝ ቶሌራ ዲንቃ ተገኝተዋል

በአሁን ሠዓት ወራቶችን የዘለቀው የሁለቱ ጀግኖች አትሌቶች ፀብ መቋጯ አግኝቶ ከረዥም ጊዜ በኃላ በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ገበታ እየተቋደሱ ይገኛሉ።

ሁለቱ የሀገር ሀብቶችና ባለታሪኮች እንዳይታረቁ ሲደክሙ የነበሩ ሠዎች በዕርቁ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ከመውደቃቸውና ከመበሳጨታቸው ሌላ የሁለቱን ፀብ ለግል ፍላጎታቸው መጠቀሚያ ለማድረግ ሲያደርጉት የነበረው ሴራም እንደከሸፈባቸው ነው ማወቅ የተቻለው።

በሁለቱ ጀግኖቻችን የእርቅ ሂደት ዙሪያ ምን ተፈጠረ?የትናንቱ እርቅ እንዳይካሄድስ የማን ረዥም የጥፋት እጅ ነበር?በዕርቁ ወቅትስ ምን ተባባሉ በሚለው ዙሪያ እመለስበታለሁ።

የሁለቱ ሠላም መሆን እንቅልፍ ያሳጣችሁ በሙሉ ሠላም በመውረዱ እንኳን ደስ አላችሁ!!




10 comments

Fasil Tesfaye October 4, 2024 - 3:15 pm

Alememaree Deguuu

Reply
Bruk Endale October 4, 2024 - 3:22 pm

ጎበዝ ጀግናው ሀይሌ ገብረስላሴ ስላስታረካቸው

Reply
በእምኔ ነኝ የቅዱስ October 4, 2024 - 3:24 pm

የአሼ ጉዳይ እንዴት ሆነ🙄🤣

Reply
Jara Diribsa Debela October 4, 2024 - 3:26 pm

በነካ እጃችሁ ሶስቱን ብሔር አስታርቁልን

Reply
Eden Liul October 4, 2024 - 3:28 pm

አሪፍ ነው 😍

Reply
Muluken Mekuria October 4, 2024 - 3:30 pm

ኢቲዮጲያዊነትን ባላበሰ መልኩ ሁሉም ሲታረቅ ለስፖርቱ መልካም ነው።🤙🤙🤙 ቀጣይ ክ.ዶ/ር ሀይሌ ገ/ስላሴ እና…..🤙

Reply
Melese Sinkie October 4, 2024 - 3:31 pm

ሀይሌ ገ/ስላሴ ሺ ዓመት ኑርልኝ እንዲህ ነው አዋቂነት

Reply
መስፍን ተስፋዬ October 4, 2024 - 3:35 pm

ደራርቱን ከተጠያቂነት ለማውጣት እና በጥምረት አሸብርን ለመጣል ይመስላል ይሄ ነገር

Reply
Fasika Daniel October 4, 2024 - 3:38 pm

They took it too far.

Reply
George Busch October 4, 2024 - 3:39 pm

ጨንቆን ነበር
ሀሳብ ሊገለን ሲል ደረሱልን

Reply

Leave a Comment