banner

በዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው ህወሓት አቶ ጌታቸው ረዳ ጨምሮ 13 የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ባለስልጣናትን ከስ

በዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው ህወሓት አቶ ጌታቸው ረዳ ጨምሮ 13 የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ባለስልጣናትን ከስልጣናቸው እንዲወርዱ መወሰኑን አስታወቀ።

በቅርቡ ጉባኤ ያደረገው ይህ የህወሓት ቡድን በምትካቸው የሚሰሩ ያላቸውን አዳዲስ ሹመቶችንም ሰጥቷል።

ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በሊቀመንበርነት የሚመሩት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ቡድን ዛሬ እንዳስታወቀው መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ/ም ባደረገው የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ህወሓትን ወክለው በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ያሉ ባለስልጣናት ከሓላፊነታቸው እንዲወርዱ መወሰኑ ይፋ አድርጓል።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ ሃምሳ ሲደመር አንድ ድርሻ እንዳለው የገለፀው የህወሓት ቡድኑ፥ ህወሓትን ወክለው በግዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ፣ የዞን አስተዳደር እና ኤጀንሲዎችና ኮሚሽኖች ያሉ ባለስልጣናት መቀየሩን አስታውቋል።

በዚህ መሰረት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ እንዴት እና በማን ይተካሉ የሚለው ከፌደራል መንግስቱ እና ከሚመለከታቸው አካላት በመግባባት ይፈፀማል ሲል ህወሓት ዛሬ ባወጣው መግለጫው ይፋ አድርጓል።

ከዚህ በተጨማሪ አቶ በየነ ምክሩ፣ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት፣ ዶክተር ሓጎስ ጎደፋይ ጨምሮ ሌሎች በህወሓት ውክልና ወደ ግዚያዊ አስተዳደሩ የገቡ ባለስልጣናት ማውረዱን የገለፀው የፓርቲው መግለጫ በምትካቸው ደግሞ እነ ዶክተር አብርሃም፣ አቶ አማኑኤል አሰፋ፣ ዶክተር ፍስሃ ሃፍተፅዮን እና ሌሎችን ለተለያዩ ሐላፋነቶች መሾሙ ያትታል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባላት እና ሌሎች በቅርቡ አካሂደውት በነበረ “ህወሓት ማዳን” የተሰኘ ስብሰባ፥ ጉባኤ ያደረገው ህወሓት በሕገወጥነት ፈርጀው በቅርቡ ሌላ ጉባኤ እንደሚያደርጉ ገልፀው እንደነበረ ይታወሳል።

ዘገባው የዶቼ ቬለ ነው።

10 comments

Hunde Sololo Tsegaye October 7, 2024 - 1:37 pm

Ye Torenet antena D/tsion 🙆

Reply
KinAfrica Hassen October 7, 2024 - 1:37 pm

ስልጣን፣
የተረገመ ስልጣን!!
የእውነት ለህዝብ ቢሆንኮ ጥሩ ነበር።

Reply
Hayat Nigus October 7, 2024 - 1:38 pm

በቃ ደሞ የድሃ ልጅ ማለቁ ነው 🤦‍♀️

Reply
Shibiru Dingo Binko October 7, 2024 - 1:45 pm

#ፈጣር ሆይ መቼ ነው ይህ ቀንበረ ከህዝቡ ጫንቃ ሚነሳው?

Reply
Eyob Eyob October 7, 2024 - 1:45 pm

ደጺ ጀግና 💪

Reply
Abessa Andent October 7, 2024 - 1:48 pm

ዳግም ለደብሬጲዮን የምሞት ትግራዋይ የለም።

Reply
Haylat Abrha October 7, 2024 - 1:48 pm

ዘሪኪ ዘሪኪ ናባይ ዶ በለ ዘርኩም ላብ ጎይታኹም እወ ገና

Reply
Mnlwal Brhan October 7, 2024 - 1:50 pm

ያኔ እንገኛለን🤣

Reply
Girazimach Haile Berhe October 7, 2024 - 1:53 pm

አየ እነ ዶ/ር ደብረጽዬን ያኔ ያኔኔኔ ከመስከረም 30 በኃላ መንግስት የለም በሚል የተነሳው ቀውስ ስንቱን አጥፍቶ በዛው ያልጠገቡ አሁንም ምን ዓይነት እልቂት እንደደገሱብን ፈጣሪ ይወቀው’ ሾተላዬች

Reply
Kirubel Tarekegn October 7, 2024 - 1:58 pm

ደህና የተረጋጋውን ሰው ሊያበጣብጡ ነው እንግዲህ …..የትግራይም ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምን ነው ሚፈልገው ሰላም ስጡን እስኪ

Reply

Leave a Comment