0
በአዲስ አበባ ባለፈው ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ቀጥሎ አሁንም ዳግም መከሰቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቢሲ አረጋግጠዋል።
ዛሬ ጠዋት 1 ሰዓት ከ37 ደቂቃ ከ50 ሴኮንድ ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱንም ተናግረዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ባለፈው በተከሰተበት አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ እነደሆነም ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቢሲ ሳይበር አረጋግጠዋል።
ሰሞኑን በተደጋጋሚ በአካባቢው የመሬት መንቀጥቀጥ እንቅስቃሴው እንዳልቆመ የተናገሩት ዶክተር ኤሊያስ ለከፋ ችግር የሚያጋልጥ እንዳልሆነም ተናግረዋል።
ለመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት የሆነው ቅልጥ አለት መሬት ውስጥ መምጣቱ መሆኑ የተናገሩት ዶክተር ኤሊያስ ይሄው እንቅስቃሴ ወደላይ አለመወጣቱን ነው የተናገሩት።
ላለፉት 19 ተከታታይ ቀናት ያህል ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን እና አሁንም ያለውን ሁኔታ እየተከታተልን ነው ብለዋል ዶክተር ኤሊያስ።

10 comments
በዚ አጋጣሚ ዲሽ የተበላሸባቹ በውስጥ አውሩኝ
ከባለፈው መለስ ያለ ነው የዛሬው!!
ያስቀየምኳችሁ ሰዎች ይቅርታ አርጉልኝ ምን አልባት ከሞትን🥺
አርሰናል ዋንጫ ሳይበላ ብቻ ጉድ እንዳንሆን 😢😭👍
እኔ ባሌ እየጨቀጨቀኝ ስለነበረ ምንም አልሰማሁም የሱ ጭቅጭቅ ራሱ ንዝረት ነው
ወደ ሳይንሱ ብቻ ከመሮጥ ። ለፈጣሪ እንስጥ
ዘንባባዎቹ ምንም አልሆኑም አይደል …. 🌴🌲
The coming of our lord JESUS CHIRIST is at hand.
ትኩረት ሁሉ ወደ ኢያሱስ✝️🙏
የምድራችን የሠላም እጦትና ክፋት የሚታየው በገፃታችን ሳይሆን በመሬት ውስጥ ንዝረት ነው ተመልሶ የሚመጣልን።
ሠላምምምምምምምምምምም