0
ይህን ተከትሎ ቴክኖ ኢትዮጵያ ከሴንቸሪ ሲኒማ ጋር በመተባበር ታዳሚዎች አዲሱን ስፓርክ 30 እና ተያያዥ የቴክኖ አዳዲስ ምርቶችን በቅርበት እያዩ አዲሱን ትራንስፎርመርስ ዋን ፊልም የሚመለከቱበት የማስተዋወቂያ ፕሮግራም አዘጋጅቷል፡፡
በሁነቱ ከ1 ሺህ በላይ ተጋባዥ እንግዶች የፊልም አድናቂዎች ፣ የቴክኖሎጂ እና የቴክኖ ተከታዮች የተገኙ ሲሆን አዲሱ የስፓርክ 30 ስልክ እና ተያያዥ የቴክኖ አዳዲስ ምርቶች ለታዳሚዎች በቅርበት ለዕይታ ቀርበዋል፡፡
ስፓርክ 30 ለየት ካለ ዲዛይኑ ባሻገር 5000 ሚሊ አምፒር ባትሪው፣ የMediaTek D6300, ፕሮሰስሩ፣ የ5G ኔትዎርክ ማስጠቀም መቻሉ፣ በውሀ አና አቧራ በቀላሉ የማይበላሽ መሆኑ እና ኩልል ያለ ድምፅ ያላቸው ስፒከሮቹ በተለይም በወጣቱ ዘንድ ተመራጭ ስልክ ያደርገዋል፡፡
በማስተዋወቂያ ፕሮግራሙ ለታዳሚዎች የተለያዩ ጨዋታዎች የተዘጋጁ ሲሆን በርካታ ስጦታዎችም ተበርክቷል፡፡ ቴክኖ ቴክኖሎጂን ከመዝናኛው አለም ጋር አብሮ በማስኬድ እና በተለይም ወጣቶችን አሳታፊ በሆነ መልኩ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ምርቶችን ማስተዋወቁን ይቀጥላል፡፡




