banner

በኮሪያ ሲካሄድ የቆየውን የእውቅና የስልጠና ፕሮግራም አጠናቀው ለተመለሱት ለእነ ግራንድ ማስተር ሄኖክ አቀባበል ተደረገላቸው

#FastMereja l ሳኦል የኩነቶች አዘጋጅ ከሌጀንድ ፐሮ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ኢትዮጲያን አፍሪካን ወክለው በኮሪያ ሲካሄድ የቆየውን የእውቅና የስልጠና ፕሮግራም አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ለተመለሱት ለእነ ግራንድ ማስተር ሄኖክ በትላንትናው ዕለት ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በቦሌ አለማቀፍ ኤርፖርት ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

በቆይታቸው ግራንድ ማስተር ሄኖክ 8ኛ ዳን ያገኙ ሲሆን በተጨማሪም በአለም የአፍሪካ ቴኳንዶ ተጠሪ ሆነው ተሹመዋል ማስተር ዘራሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ቴኳንዶ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸውን ገልጸዋል።

ማርሻል አርቱን ለማሳደግ ከባለሞያዎች ጋር ተባብረን ለመስራት ዝግጁ ነን ከዚህ በፊት የተሳሳቱ መረጃዎች በፌደረሸኖች ይወጡ ነበር አሁን ግን ይህ እንዲሆን አንፈልግም ዘርፉን ለማሳደግ ትልቅ ፕሮጀክት ይዘን መጥተናል ይህም አካል ጉዳተኞችን ሴቶችን ህፃናትና ወጣቶች ላይ ትኩረታቸውን እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

ኮሪያ ስለነበራቸው ቆይታ ተጠይቀውም ኮሪያና ኢትዮጵያ ስላላቸው ወዳጅነት በጥናት አስደግፈው እንደተናገሩ እና እሳቸው አያታቸው የኮሪያዘማችም መሆናቸውን በመግለፅ ለሀገሬ ምስክር በመሆኔ ኩራት ተሰምቶኛል እነሱም ይህን ፕሮግራም የኮርያ ፕሬዚደንት እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሌሎች የመንግስት አካሎች ድጋፋቸውን የክብር አበባ በመላክ መቀበላቸውን ጨምረው አስረድተዋል።

በቴኳንዶ ዘርፍ የአለም ተጠሪ እንደመሆናችን ማሻልርቱንም ለመስራት ለሚፈልግ ሰው በአእምሮ በአካል በአካዳሚክ እውቀት አሰልጥነው ለማብቃት ከመቸውም በላይ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።





1 comment

Ato Negera October 14, 2024 - 6:35 pm

ሳትጠፏ ምነው ማስተር😏

Reply

Leave a Comment