banner

በ100 ሺህ ብር ጉቦ ስትደራደር የነበረችው የገቢዎች ቢሮ የታክስ ኦዲት ባለሙያ በቁጥጥር ስር ዋለች

#FastMereja የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የታክስ ኦዲት ባለሙያ ሙስና ስትፈፅም እጅ ከፍንጅ ተይዛ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር መዋሏን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የጽህፈት ቤቱ ባለሙያ የሆነቸው አማረች በላቸው ማሞ ለግብር ከፋይ ግለሰብ ክሊራንስ ለመስጠት በ100 ሺህ ብር ጉቦ ስትደራደር ጥቆማ እንደደረሰው ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

በደረሰው ጥቆማ መሰረት ክትትል በማድረግ 50 ሺህ ብር ቢሮ ውስጥ ስትቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዛ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አመልክቷል።

6 comments

Mahammi King Bati October 17, 2024 - 11:41 am

እ 😳😳

Reply
Mekedi Mekedi October 17, 2024 - 11:42 am

ከህዝቡ በስተቀር ባለስልጣኑ እንዳለ ሌባ መሆኑ የታወቀ ነው

Reply
Èyū Ña October 17, 2024 - 11:42 am

ክፍፍል ላይ አልተስማሙም ይሆናል

Reply
Jere Miah October 17, 2024 - 11:42 am

ምን ያህል ቢቸግራት ነው 100ሺ የምትቀበለው…🙄

Reply
እዮብ መኮንን October 17, 2024 - 11:42 am

ይሄኔ ቶሎሳ በሰራው ጥፋት ነው እሷ ላይ የተላከከው

Reply
Mnlwal Brhan October 17, 2024 - 11:42 am

Kegna Sefer snt ale 🤣

Reply

Leave a Comment