banner

በራይድ መንደር የግንባታ ቦታ ጉብኝት ተካሄደ

#FastMereja I የራይድ ትራንሰፖርት ከፍተኛ አመራሮች፣ ከሰዋሰው መልቲሚዲያ እና ኦቪድ ሪል እስቴት የተውጣጡ ባለሙያዎችና የማኔጅመንት ቡደን ዛሬ በገላን ጉራ መንደር ተገኝተው የራይድን መንደር የግንባታ ቦታን ጎብኝተዋል፡፡

የጉብኝቱ ዓላማ የራይድ መንደር የልማት ፕሮጀክት እድገትን መገምገም ፣ ቁልፍ የግንባታ ቦታዎችን ምልከታ ማድርግ እና በራይድ እና ኦቪድ ቡድኖች መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው።

ጉብኝቱ በአጠቃላይ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች የተዋቀረ ሲሆን በእያንዳንዳቸው የጉብኝቱ ሂደትም መልካም ተሞክሮዎች የተቀመሩበት እና የልማት ጥረቶችን በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ለመመለክት ዕድል ተገኝቷል፡፡

1ኛ. የራይድ መንደር የግንባታ ቦታን መመልክት ሲሆን በዚህ የጉብኝት ክፍል ለራይድ መንደር ግንባታ የተመደበውን 90,000 ሜ² በአጠቃላይ የ9 ሄክታር መሬት ለልማት መመቻቸቱን እና ለግንባታው ዝግጁ መሆኑን መመልከተት የተቻለ ሲሆን በዚህ የመኖሪያ መንደር የራይድ አሽከርካሪዎችና ቤተሰቦች ቀደም ሲል ውል በተገባው መሰረት በሚመቻችላቸው አሰራር የመኖሪያ ቤት በቅናሽ እና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ እንደሚገነባላቸው ግንዛቤ ተወስዷል፡፡ ይህ የግንባታ ቦታ በትላልቅ አውራ ጎዳናዎች ዲዛይን የተደረገ ከመሆኑም በላይ በወንዞችንና ደኖችን እንዲሁም ውብ በሆኑ የተፈጥሮ መልክዓ-ምድሮች ያጌጠ ነው። በጉብኝቱ የመንደሩን የመግቢያና መውጫ በሮችንም መመልከት የተቻለ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በቅርቡ ወደ ግንባታ እንደሚገባ አጽንኦት ተሰጥቶበታል።

2ኛ. እንደ አጠቃላይ ኦቪድ ሪል እስቴት በገላን ጉራ እየገነባቸው የሚገኙ የመኖሪያ ቤቶችን መመልከት ሲሆን በዚህ የጉብኘት ክፍል በመኖሪያ መንደሩ እየተገነቡ ያሉ መሰረተ ልማቶችን መመልከት ተችሏል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ለምሳሌ ለእንግዳ መቀበያ፣ ለሽያጭ ክፍል፣ለስብሰባዎች እና ለልዩ ልዩ ስልጠናዎች የሚሆኑ አዳራሾችን እንዲሁም የመንደሩን የመውጫና መግቢያ በሮችንም መጎብኝት ተችሏል፡፡

3ኛ. ኦቪድ እየገነባቸው የሚገኙ የተመረጡ ፕሮጀክቶችን የእድገት ደረጃ መመልከት ሲሆን በዚህም ኦቪድ ከተማ 1 እና 2 በተሰኙ መንደሮቹ እያከናወናቸው የሚገኙትን ግንባታዎች የምልከታ ቡድኑ ተመልክቷል፡፡ በዚህ ቡድኑ የተለያዩ የክፍል መጠን ያላቸውን መኖሪያ ቤቶች በባለ12 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ ላይ የተመለከተ ሲሆን የግንባታውም ሂደት፣ጥራትና በምን ዓይነት ቴክኖሎጂዎች እየተገነባ እንደሚገኝ በአካል ለማየት ችሏል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የራይድ ትራንስፖርት ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሳምራዊት ፍቅሩ ይህ ጉብኝት የራይድ መንደርን ራዕይ እውን ለማድረግ ወሳኝ እርምጃ መሆኑ እና ፕሮጅክቱም የራይድ አሽከርካሪዎችንና ቤተሰቦችን የሚጠቅም ከመሆኑም በላይ እንደአገር ዘመናው ከተማን እና ምቹ የመኖሪያ መንደርን በመገንባት ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡

በመስክ ምልከታው ከሁለቱም ድርጅቶች ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን በቀጣይም ፕሮጀክተን ለመምራት በሚያስፈልጉ ግብዓቶች እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጎ ፕሮጅከቱ በአጭር ጊዜ ግንባታው እንደሚጀመር አረጋግጠዋል፡፡




8 comments

Elias Bekele October 23, 2024 - 3:50 pm

ባዶ ቦታ እኮ ነው የምን መንዴር

Reply
ሙሪድ ኢጄንሲ October 23, 2024 - 3:50 pm

ከራይድ ተቛም ወንድ የለም እነዚህ fiministochi

Reply
Abraham Dejene October 23, 2024 - 3:52 pm

አታስቁን

Reply
ሙሌ የወይኗ ልጅ October 23, 2024 - 3:55 pm

ወይዘሮ ሳምራዊት ፍቅሩ መንደሮቹ ኢማጅኔሽን ናቸው ወይ ……

የራይድ ሹፌሮች ጫካ ለጫካ እንዲሰሩ ግንዛቤ ማስጨበጫ ብታዘጋጁ ባይ ነኝ

የግል ሀሳቤ ነው
ከፈረስ ትራንስፖርት …..

Reply
Ma New October 23, 2024 - 3:56 pm

ለምን ባለ 12 ፎቁን አታሳዩንም ሠፈሬ እዛው አካባቢ ነው ምንም አየር የለም

Reply
Julian Tefera October 23, 2024 - 3:58 pm

ዘጠናምት በመቶ ሴት ሰራተኞች እንደሆኑ የድርጅቱ ባለቤት ወይዘሪት ሳምራዊት ስትናገር ነበር ለምን ሆኑ? ራሷ ትመልስ

Reply
Jemal Seid October 23, 2024 - 3:59 pm

ጀግኒት

Reply
Hanna Abiti October 23, 2024 - 4:01 pm

😀😃😂😂😂😂

Reply

Leave a Comment