0
እስራኤል ከእኩለ ለሊት ጀምሮ በኢራን ወታደራዊ ተቋማት ላይ ተደጋጋሚ የአየር ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች።
ኢራንም በበኩሏ ንጋት ላይ እንዳስታወቀችው በዋና ከተማዋ ቴህራን፣ ኹዜስታን እና ኢላም በተባሉ ግዛቶቿ ውስጥ የሚገኙ ወታደራዊ ሰፈሮች የእስራኤል ጥቃት እንደተፈጸመባቸው አስታውቃለች።
የእስራኤል መከላከያ ኃይል ጥቃቱን የፈጸመው ኢራን እና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ አጋሮቿ የሆኑ ታጣቂ ቡድኖች ለፈጸሙት “ለወራት የዘለቀ ጥቃት” ምላሽ መሆኑን አስታውቋል።
የእስራሌል መከላከያ ኃይል ጥቃቱን የፈጸመው “በተመረጡ ወታደራዊ ዒላማዎች” ላይ መሆኑን አስታውቆ፣ ኢራን ካለፈው ዓመት መስከረም 23/2016 ዓ.ም. ጀምሮ “ያለማቋረጥ እስራኤል ላይ ጥቃት ስትፈጽም ቆይታለች” ሲል ወንጅሏታል።
ከመከላከያ ኃይሉ መግለጫ ቀደም ብሎ የኢራን ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን በዋና ከተማዋ ቴህራን እና አካባቢው በርካታ ፍንዳታዎች መድረሳቸውን አስታውቆ ነበር።
የእስራኤል የቅርብ አጋር የሆነችው አሜሪካ በበኩሏ ጥቃቱን “ራስን የመከላከል ተግባር” መሆኑን ገልጻለች ሲል ቢቢሲ ነው ያስነበበው

10 comments
አየን እኮ ኢራን እንዴት እንዳከሸፈችው ምንም ጉዳት ሳያደርስ 😂😂😂
ቀልደኞቾ ናቸው
ሁለቱም በሰው ነፍስ ይጫወታሉ !
ሰላም ለምድራችን
ሰላም ለሰው ልጆች ሁሉ❤
ምን አገባን እኛ
መቼ መታቻትና አየንኮ #የእስራኤልን ሀያልነት ያ ሁሉ ድንፋታ #የኑኩሌር ጣቢዋም አይቀረኝ ስትል የነበረችዋ እስራኤል አሁን የላከቻቸው መሳሪያወች ሁሉ በቲህራን ሰማይ ላይ ሲሟሙ ያሳያል😂😂
እንኳን ጥቃት የተኛውን ህዝብ እንኳን አላነቃም አየን እኮ መልሱን እግዲህ ትጠብቅ
አላሁ አክበር
Let’s goooooooooo iran 🇮🇷 ጦርነቱ ተጀመረ ኢራን እስራኤልን ታጠፋታለች✌️😎
ሰበር !
እስራኤል በኢራን ላይ የአፀፋ ጥቃት ፈፅማለች።
ይሁን እንጅ አፀፋው ” ኢራን ሆይ ተቆጥተሽ ሌላ ጥቃት እንዳትሰነዝሪብኝ እኔ በትንሹ ነው የተኮስኩት” የሚል ይመስላል።
ልክ እንደ ባለፈው ተልካሻ ጥቃት!
ኢራን ቀብረር ብላ አልፋዋለች።
ነገሩም ኢራንን መንካት ለእስራኤል ምን ያክል ከባድ እንደሆነ ያሳየ ሆኖ ተጠናቋል
😂😂😂 አቀሸፈቺው አኮ አየን አባቴ ኢራን ከምገምታት በላይ ናት ❤️❤️❤️🇪🇹🇪🇹