banner

የአርቲስቷ ሚሊዮኖችን ያስወጣዉ ስምምነት

#FastMereja I ተወዳጇ አርቲስት ሩታ መንግስትአብ ከዴሉክስ ፕሮፐርቲስ ጋር በብራንድ አምባሳደርነት በሚሊዮኖች ብር በሸራተን አዲስ ሆቴል ተፈራረመች።

ዴሉክስ ፕሮፐርቲስ በሪል እስቴት ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ የተለያዩና ቅንጡ የሆኑ አፓርትመንቶችን በከፍተኛ ጥራት በመሀል ከተማ እየገነባ ያለ ድርጅት ነዉ፡፡ ድርጅቱ ክሪል እስቴት ግንባታ ስራዎች ባሻገርም ከአስራ ስምንት (18) ዓመታት በላይ በተለያዩ የግንባታ ስራዎች ላይ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው እንደ አክሲስ ፋዉንዴሽን ስፔሻሊስት ኃ/የተ/የግል/ማህበር፤ ቪቶሪዮ ኬሚካል ኢንደስትሪስ ኃ/የተ/የግል/ማህበር እና ሻይኒንግ ስቶን ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግል/ማህበር ያሉት እህት ኩባንያ ነው፡፡

ዛሬ ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል በተከናወነዉ የፊርማ ስነ-ስርዓት ላይ አርቲስት ሩታ መንግስትአብም በተሰጣት እድል እና ክብር ከልብ መደሰቷን ገልፃ በሪል እስቴት ዘርፍ የራሳቸዉን አሻራ ለማሳረፍ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ድርጅቱን በብራንድ አምባሳደርነት እንድታስተዋዉቅ በመመረጧ ደስተኛ መሆኗን ገልፃለች፡፡





1 comment

Daniel Tadesse October 26, 2024 - 3:48 pm

ያው እንግዲ ሰቶ መቀበል ነው

Reply

Leave a Comment