#FastMereja I በአዊ ብሔሄረሰብ አስተዳደር በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ የቻጃ ክብርታ ቀበሌ ነዋሪ የሆነ ወጣት ጥሩነህ ይግዛውና የጓንጓ ወረዳ ነዋሪ ወጣት ግዛቸው ወርቅነህ የተባሉ ግለሰቦች በቻግኒ ከተማ የ05 ቀበሌ ነዋሪ የሆነውን የ12 ዓመት ህፃን ታጁ የሱፍን ጥቅምት 04 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 በባጃጅ በመውሰድ ከሰወሩ በኃላ ወደ ታጋች ቤተሰብ ስልክ በመደወል 500,000ብር /አምስት መቶ ሺህ ብር/ እንዲከፍሉ ቢጠይቁም የታጋች ቤተሰብ ከሀያ ሺህ ብር በላይ የመክፈል ሀቅም እንደሌላቸው ይገልጻሉ።
ህፃኑ በጓንጓ ወረዳ ሰሜን ደገራ በተባለው ጫካ ውስጥ ለ8 ቀናት እንዲቆይ አድርገዋል ሲሉ የአየሁ ጓጉሳ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የወንጀል ምርማራ ክፍል ኃላፊ ዋና ሳጅን አዳነ ጥላሁን ገልፀዋል።
አጋቾቹ ታጋቹን ህፃን ለ 8ቀናት የጫካ ቆይታ በኋላ ከጥቅምት 11 እስከ 15/2017 ዓ.ም ድርስ በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ በቻጃ ክብርታ ቀበሌ ከጥሩነህ ይግዛው ቤተሰብ ጋር እንዲቆይ አድርገዋል ሲሉ ያብራሩት የምርመራ ክፍል ኃላፊው ማህበረሰቡ ባደረሰው ጥቆማና የወረዳው ፖሊስ ባደረገው ክትትል ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም ቦታው ድረስ በመሄድ እጅ ከፈንጅ በመያዝ በወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል ።
የድርጊቱ ፈፃሚዎች ለገንዘብ ሲሉ ድርጊት መፈፃማቸውን አምነዋል ያሉት ዋና ሳጅን አዳነ በዚህ ድርጊት የተሳተፉ ሌሎች ተባባሪ አካላትንም በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እየሠሩ መሆኑን አብራርተዋል።
Via: ዳጉ ጆርናል
