በእንሰሳት ሃብት ልማት እና የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶች ላይ ትኩረት ያደረገው በኢትዮጵያ ቀዳሚው የእንስሳት ዘርፍ አውድርዕይ እና ጉባኤ ተከፈተ
#FastMereja I 13ኛው የኢትዮ ፖልተሪ ኤከስፖ (ኢትዮፔከስ)፣ 9ኛው የአፍሪካ እንስሳት ዓውደርዕይና ጉባዔ (አሌክ) እንዲሁም 4ኛው የአፒካልቸር እና አኳካልቸር ኢትዮጵያ ዓለምዓቀፍ የንግድ ትርዒትና ዘንድሮ የሚጀመረው የባዮ ኢነርጂ የንግድ ትርዒት ጥራት ያላቸውን የዘርፉ ዋነኛ አንቀሳቃሾች በማሳተፍ ከዛሬ ጥቅምት ከ21 እስከ 23/ 2017 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄድ ይሆናል።
ከ14 ሃገራት የተውጣጡ ከ100 በላይ ዓለምዓቀፍ የእንስሳት ሃብት ዘርፍ ተዋናዮች እና ስመጥር የሀገር ውስጥ ባለድርሻ አካላት፣ ከዘርፉ ባለሙያዎች እና የንግድ ጎብኚዎች ጋር አብሮ ለመስራት በሚሊኒየም አዳራሽ ይገኛሉ።
ለ3 ቀናት በሚካሄደው ዓውደ ርዕይና ጉባዔ አጠቃላይ የእሴት ሰንሰለቱን የሚወክሉ መሰረታቸውን በቻይና፣ ቼከ ሪፐብሊክ፡ ኢትዮጵያ፣ ፈረንሳይ፡ ጀርመን፣ ህንድ፤ ኬኒያ፡ ጆርዳን፡ ኔዘርላንድሰ፣ ስኮትላንድ፡ ቶጎ፡ ቱርክ፣ ዩጋንዳ እና አሜሪካ ያደረጉ ዓለም ዓቀፍ የዘርፉ መሪዎች እና ጠንካራ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ከንግድ ጎብኚዎች ጋር ጠንካራ የስራ ግንኙነት ለመፍጠር ያስችላል ተብሏል። በኹነቱ ከ5000 በላይ የኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ እና አለም አቀፍ ሀገራት ጎብኚዎች ይጠበቃሉ።
አዘጋጅ ፕራና ኢቨንትስ ሲሆን የንግድ ትርዒት እና የቢዝነስ ኹነቶች በኢትዮጵያ ውስጥ በማዘጋጀት እና በማማከር ስራ ላይ የተሰማራ እና ዘርፉን በእውቀት በቴክኖሎጂ እና በግብዓቶች ለመደገፍ ዓለማ አድርጎ የተቋቋመ ኃ/የተ/የግ/ማ ነው፡፡






