#FastMereja SCIENTIFIC REVOLUTION ETHIOPIA (SRE) ኢትዮጵያን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ለመቀየር እየሰራ እንደሚገኝ የድርጅቱ መስራቾች ዛሬ ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም በሐርመኒ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ።
SRE ከሰራቸው ስራዎች መካከል ኦንላይን ዲጅታል ላይብረሪ በማበልፀግ ለወልዲያ መምህራን ት/ኮሌጅ ከ4.2 ሚሊዮን ብር በማውጣት የዲጂታል ላይብራሪ ድጋፍ ተደርጓል እንዲሁም በመቀሌ ከተማ ለሚገኘው አጼ ዩሀንስ መሰናዶ ት/ቤት የዲጂታል ላይብራሪ ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።
በአጠቃላይ የዲጂታል ላይብራሪው ከ250 በላይ ትምህርት ቤቶች እና 16 ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተገጥሞ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ነው በመግለጫው የተነገረው።
ከውጪ በከፍተኛ ወጪ ተገዝተው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ረገድ ሀገራችን በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ የምታስገባቸውን የቴከኖሎጂ ምርቶችን ሀገር ውስጥ በማምረት ለወጣቶች የስራ እድል እንዲፈጥሩ ለማድረግ ባለፉት 10 አመታት ውስጥ ከፍተኛ ጥረት ስናደርግ ቀይተናል ያሉ ሲሆን ከነዚህም ምርቶች ውስጥ በAI የሚታገዝና የሚመራ የትራፊክ መብራቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት፣
የግለሰቦችን መልክ እና ምስል በመለየት የሚከፈት ባዩሜትሪክ Turnstyle በሀገር ውስጥ ማምረት፣ የዱባይን ከተማ የትራፊክ ፍሰት ያዘመኑ ዘመናዊ የትራፊክ ራዳር ቴክኖሎጂ እንዲሁም የመኪናዎችን ታርጋ ቁጥር እራስ በራሳቸው መለየት የሚችሉ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚታገዙ ቴክኖሎጂ በሀገር ውስጥ ማምረት፣ ከውጪ በከፍተኛ ምንዛሬ የሚገቡ የውጪ ምንዛሬ ማሽኖችን በሀገር ውስጥ የሚተካ ቴከኖሎጂ በሀገር ውስጥ ማምረት እንደሚገኙበት ተነግሯል።
የፊልሞች ስርቆት ለመከላከል የሚያስችል Encrypted Video Display የተሰኘ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ቴክኖሎጂ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ሲኒማ ቤቶች ላይ በመተግበር ላለፉት 5 አመታት የፊልም ስርቆትን ለመከላከል ካበረከትነው አስተዋጻኦ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል።
SCIENTIFIC REVOLUTION EARTH (S.R.E) በ ዋሺንግተን ዲሲ የዛሬ 10 አመት ጥቅምት OCTOBER 31 2014 ኢትዮጵያን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የላቀ ለማድረግ የተመሰረተ ድርጅት ነው።







1 comment
ከኔ ሂወትጋ ምን ያገናኘዋል