banner

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የስራ ክህሎት ዕድል ፈጠራ ቢሮ ለተለያዩ 98 ማህበራት የመስራያ ቦታ ለወጦቶች አስረክቧል።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ስራ አሰሪና ሠራተኛ መምሪያ ሀላፊ አቶ ታርኩ ጥላሁን እንደገለፁት በከተማዉ ከዚህ ቀደም ከነበሩ ጉድለቶች በመነሳት ክህሎት መርህ የስራ ዕድል ፈጠራን ተግባራዊ በማድረግ የሰለጠነ የተመዘነ እና መስፈርቶችን የሚያሟሉ ወጣቶችን ብቻ በአግባቡ በመለየት በመረጡበት የስራ መስክ ዉጤታማ እንዲሆኑ በርካታ ልየታዎችን አድርገን በዛሬው እለት የሚስፈልገውን ነገር አግዘናል።

የሀዋሳ ከተማን ከስራ ዕድል መፍጠር ባሻገር ዉጤታማ ተግባራትን የክህሎት ግንባታዎችን በማከናወን ከክልሉ አልፎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተማችንን የተሞክሮ ማዕከል ለማድረግ መጠነ ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አቶ ጥላሁን ግልፀዋል።

አሁን የመስሪያ ቦታዎችን ያስረከብናቸው ወጣቶችንን ያግዝ ዘንድ ለማህበራቱ የአቅም ግንባታና የክህሎት ስልጠናዎችን እንዲወስዱ ከማድረግ ባለፈ ከብድርና ፋይናንስ ተቋማት ጋር የማስተሳሰሩንም ስራ በተፋጠነ መልኩ እያመቻቸ በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል።

በ2017 በጀት ዓመት ለ14 ሺ 828 ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ያነሱት አቶ ታሪኩ በዛሬዉ ዕለትም በ98 ማህበራት ለታቀፉ 490 ወጣቶች ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የመስሪያ ቦታዎችን ርክክብ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ከማህበራቱም 28ቱ በአገልግሎት ዘርፍ፣38ቱ በኢንዱስትሪ እና 32ቱ በግብርናው ዘርፍ መሰማራታቸውን ሀላፊው አስታውቀዋል።

ማህበራቱ ለአምስት ዓመታት ብቻ ቦታዉን መረከባቸው የተናገሩት መምሪያ ኃላፊ ሰርተዉ ወጤታማ በመሆን ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪ እንዲሸጋገሩም እያገዝን የጋራ ትብብር በማደረግ ለመስራት ታቅዷል።

በመጨረሻም አቶ ታሪኩ ጥላሁን በዚህ ወቅት ለወጣቱ መጠነኛ የሆነ የስራ እድል በብዛት በመፍጠር በስልጠና እና በብድር መልክ ፋይናንስ እንዲያገን በማድረግ እራሱን እንዲያጠናክር ያስችላል ሲሉ ገልፀዋል።

በመንግስት በኩል ብቻ ሳይሆን ከበርካታ ግል ተቋማት ጋር በትብብር በመስራት ለወጣቱ የስራ እድል ለመፍጠር በትኩረት ለመስራት አቅደናልም ብለዋል።





1 comment

Dawit Cahma November 1, 2024 - 11:32 am

Tare GANA xaano atewiini lowore agareemo.

Reply

Leave a Comment