banner

በሌባ ተቀባዮችና ወንጀል ፈፃሚዎች ላይ በተደረገ ኦፕሬሽን በርካታ ሞባይሎችና የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በሌባ ተቀባዮችና ወንጀል ፈፃሚዎች ላይ በተደረገ ኦፕሬሽን በርካታ ሞባይሎችና የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከህብረተሰቡ የደረሰውን ጥቆማ መነሻ በማድረግና ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ከሌባ ተቀባዮች ላይ የተለያዩ መጠን ያላቸውን ሞባይሎችና ሌሎች ንብረቶችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

ግለሰቦቹ ህጋዊ ንግድ ፈቃድን ሽፋን አድርገው በኤሌክትሪክ ጥገና ሱቅ ውስጥ ከተለያዩ ቦታዎች የተሰረቁ ንብረቶችን ከሌቦች ላይ እየተቀበሉ እንዳከማቹ ለክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ እንዲሁም የተለያዩ ወንጀሎችን ፈፅመው በተያዙ ግለሰቦች ላይ በተደረገ ፍተሻ 148 ሞባይል፣ 45 ታብሌት፣ 29 ሪጉሌተር፣ 5 ላፕቶፕ፣ 9 ሞንታርቦ፣ 1 ጀኔሬተር፣ 1 ፍላት ቴሌቪዥንና 6 የመኪና ጎማ ከ16 ቸርኬዎች ጋር እንዲሁም ብዛት ያላቸው የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም 15 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው አስፈላጊው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የጠቀሰው ፖሊስ መምሪያው በቀጣይም የቁጥጥሩን ስራ እና ህጋዊ እርምጃ የመውሰዱን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ሞባይልና ሌሎች የተጠቀሱ ንብረቶች የተሰረቀባቸው ግለሰቦች በአቅራቢያቸው ባሉ ፖሊስ ጣቢያዎች እና በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ንብረቶቻቸውን በመምረጥ መውሰድ እንደሚችሉ ፖሊስ መምሪያው አሳስቧል።

ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት እያደረገ ያለው እገዛ ከፍተኛ እንደሆነ የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ በቀጣይም ጥቆማ ከመስጠት ጀምሮ የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

አዲስ አበባ ፖሊስ





1 comment

Dagista Dagmawit Dagi Dagista November 5, 2024 - 2:27 pm

እንደለመዳቹት ለብሄራዊ ገቢአርጉት

Reply

Leave a Comment