በአሜሪካንና በአንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት Dog walker የሚባል የስራ መስክ አለ ። በቀን ውስጥ ብዙ ብር ከሚገኝባቸው ስራዎች መሀከል አንዱ በሆነው በዚህ ስራ ላይ የሚሰማራ አንድ ሰው በሰአት ከ17 – 22 ዶላር መስራት ይችላል ።
….
ለዚህ ስራ የሚያስፈልገው መስፈርት ውሾችን መውደድ መቻል ነው ። እና በዚህ ስራ በሙሉ ጊዜ ወይም በትርፍ ሰአት ለመስራት ለመሰማራት የሚፈልግ ሰው ፡ ይህን ስራ ለሚሰጡ ድርጅቶች ጋር በመሄድ ይመዘገባል ።
እና ውሻ የሚያሳድጉ ሰወች ፡ በስራ ምክንያት ጊዜ ከሌላቸው እና ውሻቸውን እግሩን እንዲፍታታ ይዘውት ዎክ ማድረግ ካልቻሉ ፡ ወደዚህ ድርጅት አስረክበው ወደስራ ይሄዳሉ ።
……
ድርጅቱም ሰራተኞቹን አሰማርቶ ውሻውን ወክ ይዘውት ይወጣሉ ።
እና ውሻው ከተመደበለት ሰው ጋር ዎክ አድርጎ ፡ እግሩን አፍታቶ ፡ ወደቤቱ ይላካል ፡ ወይም የውሻው ባለቤት መጥቶ ይወስደዋል ።
……..
ይህ ስራ ፡ በአሜሪካን ውስጥ ብቻ. . በአመት ከአንድ ቢሊየን ሶስት መቶ ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያስገባ ፡ ትልቅ ቢዝነስ ሲሆን ለ 58,493 ሰወች የስራ እድል የከፈተ ስራ ነው ።
….
እና ይህን ይህን ስታይ ፈረንጆች ለውሾቻቸው ያላቸውን ፍቅርና የሚሰጡትን ትኩረት፡ እና እኛ ባለን አቅም ውሾችን ትሪት የምናደርግበትን መንገድ ፡ ሲታይ ፡ ለእንስሳት ያለን ነገር. . ብዙ እንደሚቀረው የሚያሳይ ነው ።
በተጨማሪም የነሱ የስራ ፈጠራ ችሎታና ፡ ለስራ ያላቸው የከበረ አመለካከት 🙏
ፀሐፊው ዋስይሁን ተስፋዬ ነው።
0

5 comments
እንኳን እንሥሣውን ሰውን መች ወደድነው ?
ጉዞው ይመቻችልን
ወይኔ በላቸው😡😡 ወይኔ በላቸው ተቃጠልን 😴
🙄🙄🙄
በአብይ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው ከመሆን አሜሪካ ውሻ መሆን የተሻለ ነው