0
#FastMereja I ካምብሪጅ አካዳሚ ኢትዮጵያ ከ53 ሀገራት የመጡ የተለያዩ ተማሪዎችን በአንድነት ይዞ የሚያስተምር ኢንተርናሽናል ተቋም ሲሆን በIGCSE ዓለም አቀፍ ፈተና በሃገር አቀፍ ደረጃ የአንደኝነት ደረጃ በማጠናቀቁ ዛሬ ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ በተካሄደ ስነ ስርዓት የላቀውን ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት አበርክቷል።
ዛሬ ሽልማት የተሰጣቸው የካምብሪጅ አካዳሚ ተማሪዎች በ82 የዓለማችን ሀገራት የተሰጠ ፈተናን ከፍተኛ ውጤት ማምጣት የቻሉ ስለሆነ ሀገራዊ ድል እንደሆነ የካምብሪጅ አካዳሚ መስራች እና ባለቤት ፕሮፌሰር ገመቺስ ደስታ ገልጿል።
በፕሮግራሙ ላይ የካምብሪጅ አካዳሚ እህት ኩባንያ የሆነው ሻሸመኔ የሚገኘው ሊድስታር አካዳሚ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከፍተኛ ውጤት ያመጡት ቶፕ 10 ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቿል።




