0
ብሔራዊ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማዕከል ዳይሬክተር ዶክተር ጸጋይ ብርሀነ ለአል ዐይን እንዳሉት ማዕከሉ ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በአጠቃላይ ለ187 ሰዎች የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና አገልግሎት አድርጓል ብለዋል።
አሁን ላይ ማዕከሉ በሳምንት እስከ ሶስት በዓመት ደግሞ እስከ 100 ሰዎች ድረስ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና የመስጠት አቅም እንዳለው የሚናገሩት ዶክተር ጸጋይ በግብዓት እጥረት ምክንያት በአቅሙ ልክ እየሰራ እንዳልሆነም ገልጸዋል።
የአካል ልገሳ ጉዳይ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ ጉዳይ ነው የሚሉት ዶክተር ጸጋይ ኩላሊታችንን መሸጥ እንፈልጋለን፣ ኩላሊታችንን ግዙን የሚሉ ዜጎች ወደ ማዕከሉ እንደሚመጡም አክለዋል።
ዘገባው የዐል ዐይን ነው።

10 comments
አያስቅም ..✍️‼️
እንደዚህ ዜና ከልቤ ያሳዘነኝ የለም።
ኧረ ድህነት አይኑ ይጥፋ!
እኔ ራሱ የሚገዛ ካገኘሁ ሸጣለሁ አንድም ሰው በኩላሊት እጦት አይሞትም✊
ስንት ነው ኣንዱ ?
እኔም ሄጄ ነበር😑
ይኼ የሚያሳየዉ ሰዋች በኑሮ እጅጉን
መቸገራቸዉን የሚያሳይ ነዉ !!! በጣም
ያሳዝናል አሁን ደግሞ በቤት ፈረሳ በንግድ ተቋሟት ፈረሳ በትራንስፖርት ጭማሪ በግብር ጭማሪ ፣
በጦርነት …………
የበለጠ እየተሰቃየ ያለ ህዝብ ነዉ ፡፡
እነሱ እየበለጸግን ነዉ እያሉ ነዉ !
ጌታ ሆይ ህዝብህን አስብ🙏😭
አቤቱ ጌታ ሆይ አገራችንን በምህረትህ አስባት።በጣም የምያሳዝን እና የሚያስለቅስ ነገር ነው እንጅ የሚቀለድ ነገር አይደለም።
አዎ ግዙን በዚህ ዘመን ሁለት ኩላሊት ሁሉ ምን ያደርግልናል🥺
እነሱ ሽጠው ማን ሊኖርበት 🙆😳