banner

በሱፍቃድ ሪል እስቴት ከሁለት የፋይናንስ ተቋማት ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

#FastMereja I ከተመሰረተ ገና የሁለት ዓመታት ዕድሜ ያለውና በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ እየተገነባ ያለው በሱፍቃድ ሪል እስቴት ከአማራ ባንክ አ.ማ እና ከአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ጋር በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከዋና ዋና ከተሞች ወጣ ብሎ ወረዳዎችንና አዳጊ ከተሞችን በማነቃቃት፣ የኢንዱስትሪ ልማት ፍሰቶቻቸውን የሚያግዝ፣ የማኅበረሰቡን አኗኗር (Housing Lifestyle) በማዘመን የከተማ ልማት እያፋጠኑ ከሚገኙ ጥቂት ፕሮጀክቶች ቀዳሚ ነው። ይህ በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ እየተገነባ ያለው አዲስ የመኖሪያ መንደር ለቤት ደንበኞቹ አስተማማኝ የቤት ግንባታ አገልግሎት እና የፋይናንስ አቅርቦት የሚያግዝ ስምምነት ነው ከሁለቱ ግዙፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም በአረርቲ ከተማ የተፈራረመው።

ስምምነቱን የበሱፍቃድ ሪል እስቴት ልማት ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚና የኩባንያው መሥራች አቶ በሱፍቃድ ተስፋዬ፣ “ሁለቱም የፋይናንስ ተቋማት የሪል እስቴት ኩባንያና ለቤት ደንበኞቹ የፋይናንስ አቅርቦት ላይ ግንባር ቀደም አጋር ሲሆኑ፣ እንደ በሱፍቃድ ሪል እስቴት ያለ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ጋር በመሥራት ፋይናንስን ለስትራቴጂያዊ ልማት እያዋሉ ስለሚገኙ አብረን በመስራታችን ኩራት ይሰማናል” ብለዋል በስምምነቱ ወቅት።

የበሱፍቃድ ሪል እስቴት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምንጃር ሸንኮራዋ አረርቲ ከተማ ስትጠራ ስሙ አብሮ የሚነሳው ሲሆን በ230,000 ካሬ ሜትር ላይ 1,000 ቤቶችን፣ ባለ 5 ኮኮብ ሆቴል፣ ከአጸደ-ሕጻናት እስከ ኮሌጅ ድረስ ደረጃውን የጠበቀ የትምህርት ተቋም እና የጤና ተቋማት፣ ለስምጥ ሸለቆዋ የቱሪስት መዳረሻ አረርቲ ተስማሚ የመዝናኛ ስፍራዎችን ያካተተ አዲስ መንደር እየገነባ ይገኛል።

በፊርማው ሥነ-ስርዓት ላይ አረርቲ ከተማ የተገኙት የአማራ ባንክ አ.ማ የማርኬቲንግ እና ኮሙኒኬሽን ማናጀር አቶ ኪሩቤል ይስሐቅ እና የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ወዳጆ በጋራ የፋይናንስ አቅርቦት ላላገኙ የታችኛው የኤኮኖሚ እርከን ማህበረሰብ ክፍል ላይ ትኩረት ያደረገ የፋይናንስ አቅርቦት (access for the bottom) በማድረግ ማኅበረሰብን ለመለወጥ እንዲህ ያለ አጋርነት ቁልፍ ተግባራቸው መሆኑን አሳውቀዋል።

ከዲስ አበባ በተለይም ከደብረብርሃን ከተማ 180 ኪሎ ሜትር፣ ከሞጆ ደረቅ ወደብ እና የፍጥነት መንገድ እና ከናዝሬት በቅርብ ርቀት የምትገኘው አረርቲ ከተማ በቅርብ ዓመታት የግዙፍ ኢንቨስትመንት እና የቱሪስት መዳረሻ በመሆኗ፣ የወረዳው፣ የከተማዋ እና የአጎራባች አካባቢዎች የቤት ፍላጎትን ጥያቄ የሚመልስ የመኖሪያ መንደር መሆኑ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል። አረርቲ ከቅርብ ከተሞች ጋር ባላት የኤኮኖሚ መስተጋብርም የቤት ደንበኞች ከመላው ዓለም እና ከልዩ ልዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እየከተሙባት ትገኛለች።

የሱፍቃድ ሪል እስቴት ቤቶች ባለ 150 ካሬ፣ 200 ካሬ፣ 320 ካሬ እንዲሁም 500 ካሬ አማራጮችን በማዘጋጀት ክቡራን ደንበኞቹን እያስተናገደ ስለሚገኝ፣ የአዲሱ መንደር ነዋሪ ለመሆን በሚከተሉት አድራሻ ማግኘት ይቻላል።

0912632430
0910411282
0917772244
ዐዲስ መንደር፣ ዐዲስ አኗኗር
በሱፍቃድ ሪል እስቴት




Leave a Comment