banner

በሲዳማ ክልል በመንግስት መስሪያ ቤት ሀላፊዎች የሚሰጡት አስተዳደራዊ ውሳኔዎችም ሆኑ የሚወጡ መመሪያዎች የዜጎችን መብት እንዳይ

በሲዳማ ክልል በመንግስት መስሪያ ቤት ሀላፊዎች የሚሰጡት አስተዳደራዊ ውሳኔዎችም ሆኑ የሚወጡ መመሪያዎች የዜጎችን መብት እንዳይጥሱ የሚከለክል አዋጅ ፀደቀ!!!

የሲብክመ ፍትህ ቢሮ ከኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት በክልሉ ለሚገኙ አስፈፃሚ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሠው ሀብት ዳይሬክተሮች በአስተዳደር ስነስርዓት አዋጅ ላይ ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል።

ስልጠናውን በንግግርና በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት የከፈቱት የክልሉ ፍትህ ቢሮ ምክትል ሀላፊና የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ አሽሌ ዳንኤል ሲሆኑ የአስተዳደር ስነስርዓት አዋጁ በመንግስትና በህዝቡ መሐከል ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ ግልፅና ህግን መሠረት ያደረገ መሆን እንዳለበት ገልፀዋል።

በመንግስት መስሪያ ቤት ሀላፊዎች የሚሰጡት አስተዳደራዊ ውሳኔዎችም ሆኑ የሚወጡ መመሪያዎች የዜጎችን መብት እንዳይጥሱ የሚከለክል አዋጅ መሆኑን ገልፀዋል።

ይህ አዋጅ በአግባቡ ተፈፃሚ ከሆነ የህዝብ አመኔታ ( public Trust) የሚጨምር የአስተዳደር ፍትህንም የሚሰጥ በመሆኑ አስፈላጊ ስልጠና ሲሉ ወ/ሮ አሽሌ ዳንኤል ገልዋል።

የሲዳማ ክልል ምክር ቤትም ይህንን አዋጅ አፅድቋል::

ስልጠናው በሚኒስቴር መሥሪያ ቤት አመራር ወ/ሮ ስምረት ታደሠ እየተሰጠና ለ2 ቀናት የሚሰጥ ይሆናል::





1 comment

Herods Herods November 12, 2024 - 4:55 pm

ካድሬ ምንም ስልጠና ቢወስድ….

Reply

Leave a Comment