banner

ለናሙና ወደ ውጪ የተላኩ ማዕድናት ወደ ሀገር ቤት አለመመለሳቸውን ተሰማ

ከማዕድን ዘርፉ እና ከማዕድን አምራቾች በቂ ገቢ እየተሰበሰበ አለመሆኑን የተገለፀ ሲሆን ለናሙና ወደ ውጪ የሚላኩ ማዕድናት ወደ ሀገር ቤት አለመመለሳቸውን በተደረገው የኦዲት ግኝት መረጋገጡ ተገልጿል።

በማዕድን ሚኒስቴር ከማዕድን የሚገኝ ገቢን ማሳደጉን እና መሰብሰቡን በተመለከተ የተከናወነዉን የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ እንደተገለጸው በሚኒስቴር መ/ቤቱ ላይ የህግ ማዕቀፍ ክፍተት እንዳለበት በመጥቀስ ለአብነትም የአለኝታና የአዋጭነት ጥናቶች በአግባቡ አለመደረጋቸው ይገኙበታል ብሏል።

ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዳለዉ ለናሙና ወደ ውጪ የሚላኩ ማዕድናት ወደ ሀገር ቤት አለመመለሳቸው እና በተቋሙ በኩል ግን የተሰጠው ምላሽ አጥጋቢ አይደለም ሲል አስታውቋል

ይህም ለሀብት ብክነት የሚዳርግ ነዉ ያለዉ ቋሚ ኮሚቴዉ ማዕድናቱ የሚመለሱበትን ስርአት መዘርጋት ይገባል በማለት አሳስቧል።

በማዕድን ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ሚሊዮን ማቲዮስ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት በክዋኔ ኦዲት የታዩ ክፍተቶችን ለማረም የሚያስችል አዲስ አደረጃጀትና አሰራር እንዲሁም የአዋጅ ማሻሻያ መዘጋጀቱን ገልፀዋል ሲል ካፒታል ነው የዘገበው።

5 comments

Biruk G Desalegn November 14, 2024 - 9:50 am

እኔንም ለናሙና ውጪ ቢልኩኝና እዛው ቢያስቀሩኝ 🙌

Reply
Sintayehu Kebede November 14, 2024 - 9:50 am

የስው ሲገርመን ግኡዝ እቃ አልመለስ አለ

Reply
Lëãlëm St Gëørgë November 14, 2024 - 9:50 am

መመለሻ ትኬት ካልተቆረጠላቸውስ😎

Reply
ፍቅር ያሸንፋል November 14, 2024 - 9:51 am

በዛው አሜሪካ ሔደው ጥገኝነት ጠይቀዋል ሲል fna tv ዘግቦዋል፡፡

Reply
Mame ET November 14, 2024 - 9:51 am

ይቺ አስቂኝ ሀገር😂

Reply

Leave a Comment