banner

ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ሴት ተማሪዎች ሽልማት ተሰጣቸው።

#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2016 የትምህርት ዘመን በሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ሴት ተማሪዎችን እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ከኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ሴት ተማሪዎች ዛሬ ሕዳር 05/2017 ዓ.ም በፍሬንድሺፕ ሆቴል በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ሽልማት ተበርክቶላቿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይንእሸት ዘርይሁን ለተማሪዎቹ እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ ጠቃሚ መልዕክት አስተላልፏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ሁለተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማጎለበት የማህበረሰቡን ንቃተ ህሊና ሊያጎለብቱ የሚችሉ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተነገልጿል።

በትምህርቱ ዘርፍ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ሴቶችን ማበረታታትና እወቅና መስጠት በወጣት ሴቶችና በሌላው ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግ ጠቃሚ መሆኑ ተነግሯል።



1 comment

Marko Polo November 14, 2024 - 2:02 pm

ለምን ትላያዩናላቹሁ

Reply

Leave a Comment