banner

የተባበሩት መንግስታት በኢትዮጵያ በትዳር ውስጥ የሚፈጸም አስገድዶ መድፈር በወንጀል እንዲያስቀጣ ጠየቀ።

#FastMereja I የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፤ በኢትዮጵያ በትዳር ውስጥ የሚፈጸም አስገድዶ መድፈር በወንጀል እንዲያስቀጣ ፣ የሞት ቅጣት እንዲቀርና ሕጻናትን ለውትድርና መመልመል እንዲቆም ጠየቀ

የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ትናንት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ባደረገው ግምገማ በርካታ አገራት አሳሳቢ ባሏቸው የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ዙሪያ ለኢትዮጵያ ምክረ ሃሳቦችን ሰጥተዋል።

ከምክረ ሐሳቦቹ መካከል፣ የሞት ቅጣት እንዲቀር፣ በትዳር ውስጥ የሚፈጸም አስገድዶ መድፈር በወንጀል እንዲያስቀጣ ኾኖ እንዲደነገግና ሕጻናትን ለውትድርና መመልመል እንዲቆም የሚሉት ይገኙበታል።

በጋዜጠኞች፣ በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ በሲቨክ ማኅብረሰብ ድርጅቶችና በተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች፣ የአስገድዶ መሠወር ድርጊቶችና ከሕግ ውጪ የኾኑ እስሮች እንዲቆሙና በጊዜያዊ ማቆያዎች የተፈጸሙ የሥቅየት ድርጊቶች በገለልተኛ አካል እንዲመረመሩም በርካታ አገራት ምክረ ሃሳቦችን አቅርበዋል፡፡

Via ዋዜማ

10 comments

Mesfen Mulugta November 14, 2024 - 4:55 pm

ህግ ምንድነው ኢትዮጵያ ላይ ህግ አለ ቢኖር ለሄቨን ነበር 😭😭😭😭😭

Reply
ተስፍሾ የሚካኤል ልጅ November 14, 2024 - 4:55 pm

ሚስቴ በየቀኑ ደፈኝ እያለች ፖሊስ ጣቢያ እና ፍርድ ቤት ልታመላልሰኝ ነዋ 😄

Reply
Teddy Demeke November 14, 2024 - 4:55 pm

የተባበሩት መንግስታት በኔ ሚስት ምናገባው 😂😂😂

Reply
Abie Tefera Tarekegn November 14, 2024 - 4:56 pm

?

Reply
Helen Solomon November 14, 2024 - 4:56 pm

መጀመሪያ የህፃናቱን መደፈር እና መሞት ይቃወም ደሞ መደፈር መደፈር ነው ከፋፍሎ መቃወም የለም

Reply
Wendya Sisay November 14, 2024 - 4:56 pm

አገራችን ላይ ስንት የሚያሳስብ ጉዳይ አለ ለናንተ ይሄ ነው ሚያሳባቹ የሰው ሞትስ አያሳስባቸውም

Reply
Bini Addis November 14, 2024 - 4:56 pm

ኢትዮጵውያን እየገማችሁኝ ነው ዜግነት መቀየር እፈልጋለሁ

Reply
Zerihun Mekonen November 14, 2024 - 4:56 pm

ህጻናት ሲደፈሩ በቅጡ የማይቀጣ ህግ… ስራ ባታበዙበት ምን አለ?

Reply
አብዱ ከድር November 14, 2024 - 4:57 pm

የሞት ድርጅት

Reply
ቢንያም ዋና November 14, 2024 - 4:58 pm

ስጀመር ሚስት ማግባት ግዜው ያለፈበት ጎጂ ልማድ ነው 🤣

Reply

Leave a Comment