banner

ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ አክሰም አይጓዙም

የኅዳር ጺዮን ዓመታዊ ክብረ በዓልን በማስመልከት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወደ ርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጺዮን እንደሚጓዙ ተደርጎ በተለያዪዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወር የሰነበተው ዜና ፍጹም መሰረተ ቢስና በቅዱስ ፓትርያርኩም ሆነ በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል ወደ ርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ለመጓዝ የተያዘ ምንም አይነት መርሐ ግብር አለመኖሩን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ምንጮቻችን አረጋግጠውልናል።

የቅዱስነትዎ ቡራኬ ይድረሰን።

10 comments

እዮብ መኮንን November 14, 2024 - 6:16 pm

ምነው !? ለምን ኣይጓዙም

Reply
Tamrat Alemu Tamrat November 14, 2024 - 6:18 pm

እኚህን አባት ለምንድነው የሚያወናብዱት?

Reply
Meme Fiker November 14, 2024 - 6:20 pm

አሜን

Reply
Ghirmay Teklle November 14, 2024 - 6:22 pm

ገደል ይግባ ሲፈልግ

Reply
Tagel Tadele November 14, 2024 - 6:23 pm

ፖለቲካ ኢዝ ደርቲ ጌም ያለው ማን ነበር😭

Reply
አማኑኤል አባቴ አማኑኤል November 14, 2024 - 6:23 pm

አሜን 🙏🙏🙏

Reply
Teklay Gebretsadkan November 14, 2024 - 6:25 pm

ኣቤት ያኔ ጁንታ ጀነራል እንዳላላችዋቸው ኣሁን ብፁዕ ወቅዱስ ወደ ኣክሱም ህዳር ፅዮን ለማክበር ኣይሄዱም ስትሉ ቢያንስ ህሊናችሁ ኣይወቅሳችሁም።ሲኖዶስ እንደዛ ሲያወክባቸው እሳቸው የተናገሩት የግላቸው እንጂ ሲኖዶሱን ኣይወክሉም ሲሉ እንዳልነበር አሁን ግን ወደትግራይ ሲሆን ኣባታችን ማለት ነውር ነው።እንዳላችሁት በግላቸው ይሄዱ ይሆን።

Reply
ብሩክ ገዳም የማርያም ልጅ November 14, 2024 - 6:26 pm

ቅዱስ ፓትርያሪኩ በአንድ መንበር፣በአንድ ሲኖዶስ፣በአንዲት ቤተክርስቲያን ስለሚያምኑ በረከታቸው ይደርብንና አይጓዙም!!!

Reply
Axum Tsion November 14, 2024 - 6:27 pm

ቢሄድስ ምድነው ችግሩ

Reply
Haylu Love November 14, 2024 - 6:27 pm

አይይይ በቃ እንደ ቦለቲካ አደረጉት አይሄዱም ማለት ምን ማለት ነው

Reply

Leave a Comment