banner

ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት ጽሩይ የሳሙናና ዲተርጀንት ፋብሪካ ተመረቀ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሲዳማ ሀገረ ስብከት በይርጋዓለም ደ/ታቦር ኢየሱስ ወደብረ መንክራት ቅድስት አርሴማ አብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤ የተገነባው ጽሩይ የሳሙናና ዲተርጄንት ፋብሪካ ተመርቋል ።

ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት ዘመናዊ ፋብሪካው ቤተ ክርስቲያን በምጣኔ ሀብት ራሷን የምትችልበትን በር የሚከፍት እንደሆነም ተገልጿል ።

ፋብሪካው የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ከማገዝ ባሻገር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ከ300 በላይ ለሚሆኑ ሠራተኞች የሥራ እድል እንደሚፈጥርም የፕሮጀክቱ ኀላፊ ዶ/ር ታደሰ ፋንታዬ ጠቅሰዋል ።

አሁን ላይ የልብስና የገላ ሳሙና እያመረተ የሚገኘው ፋብሪካው ቤተ ክርስቲያን ድህነትን ለመቀነስ በኢንዱስትሪ ልማት የሚኖራት አስተዋጽኦ ጉልህ ለመሆኑ ማሳያ እንደሆነ ተገልጿል ።

በርካታ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ የሚገኘው ሀገረ ስብከቱ ለሌሎች ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናትም በልማት ራስን የመቻልና ከልመና የመውጣትን ተሞክሮ ማሳያ እንደሆነ ተገልጿል።
ዘገባው የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ነው


4 comments

Simon Belay November 16, 2024 - 11:21 am

Hezebe eyegema neber deresachuhelet.

Reply
Ekram Klifa November 16, 2024 - 11:25 am

ኦርቶዶክሶች ተቋማት ማህበራት ማቋቋም ትችላላችሁ በጣም የማደንቅላችሁ መንግስት ከሚቀጥረው ቤተክርስቲያን የቀጠረቻቸው ይበልጣሉ ሲባል ሰምቻለሁ ይመቻችሁ !!

Reply
Mafi Mekuria November 16, 2024 - 11:25 am

we should stand by you 🙏our president 🤜💪

Reply
Netsanet Tafese November 16, 2024 - 11:27 am

እሴይ እንኳን ደስስስስ አላቹ /አለን🙏 እግዚሐብሔር ይመስገን🙏🙏🙏 ትልቅ ስራ ሰርታቹሐል እና ክብር ይገባቹሐል🙏🙏🙏

Reply

Leave a Comment