#FastMereja I የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራች እና ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ እና የዲቦራ ፋውንዴሽን ሰራተኞች ዛሬ ሕዳር 09/2017 ዓ.ም በውጪ ሀገር የሚሰጡ ህክምናዎችን በሀገር ውስጥ እየሰጠ የሚገኘውን ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ።
ሆስፒታሉ ወደ ውጭ ሀገር የሚያስኬዱ ከፍተኛ ሕክምናዎችን በሀገር ውስጥ ማከናወንን ዋንኛ ዓላማው አድርጎ መቋቋሙን ያስረዱት የሆስፒታሉ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃን ተድላ ሆስፒታሉ ሥራ በጀመረ በአጭር ጊዜ ለ32 ሕፃናት የተሳካ የልብ ቀዶ ሕክምና በነፃ ማከናወኑን አስረድተዋል፣ ይኸም በገንዘብ ሲተመን ወደ 26 ሚሊዮን ብር እንደሚገመት ተናግሯል በተጨማሪም 4ሺ ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ የቀዶ ጥገና ሕክምና አከናውኗል።
አቶ ብርሃን ከዲቦራ ፋውንዴሽን ለህክምና ወደ ውጪ መሄድ የሚያስፈልጋቸው ሁለት ህፃናትን ተቀብሎ በነፃ ለማዳከም ቃል ገብቷል። ከዚህ በተጨማሪ በፋውንዴሽኑ በመገኘት የህክምና ክትትል እንደሚያደርጉ ገልጿል።
የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራች እና ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ ባደረጉት ንግግር «ማየት እና መስማት የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው» ያሉ ሲሆን «ዛሬ በሆስፒታሉ የተመለከትናቸው በውጪ ሀገር የሚሰጡ ህክምና በሀገር ውስጥ በኢትዮ ኢስታንቡል መሰጠታቸው ለሀገራችን ትልቅ ስጦታ ነው። ይኸን ለሰራችሁ ማመስገን ፈልጋለሁ» ብሏል። «ዛሬ ለሁለት ታካሚዎች የተሰጠው ነፃ ህክምና ትልቅ ስጦታ ነው ከልብ እናመሰግናለን» ብሏል። መንግስትም ለሀገራችን ትልቅ ስጦታ ለሆነው ለዚህ ጠቅላላ ሆስፒታል ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቋል።
በቴክኖሎጂ በታገዙ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችና ከፍተኛ ልምድ ባካበቱ ከ73 በላይ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ስፔሻሊስትና ሰብ-ስፔሻሊስት ባለሙያዎች በመታገዝ ዜጎቻችንን ለህክምና ወደ ውጭ አገር በመሄድ የሚያወጡትን ከፍተኛ ወጪና እንግልት ለማስቀረት እና ውጭ አገር የሚያስኬዱ ሕክምናዎችን በሀገር ውስጥ ለመስጠት አላማው አድርጎ የተመሰረተ ተቋም ሲኾን ሲጀመር 24 የነበረው የሕክምና ዲፖርትመንት በአሁኑ ወቅት ወደ 42 አድጓል።
ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል በ10ሺ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ግዙፍ ጠቅላላ ሆስፒታል ለመገንባት ዲዛይን ሰርቶ የመሬት ጥያቄ ለመንግስት አቅርቦ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።





1 comment
❤️❤️👌