***
ፒላርሰ ትሬዲንግ መንግስት በአሁን ሰዓት እየተገበረው የሚገኘዉን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ የሚያነቃቃ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል ድርጅታችም ይህንን አገጣሚ በመጠቀም አለም አቀፍ ብራንድ ከሆነው ባታ ጫማ ጋር ስምምነት በመፈረም ብቸኛ አከፋፋይ በመሆን ወደ ኢትዮጵያ ገቢያ በማሰገባት ለሺያጭ ለማቅረብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
እ ኤ አ በ1894 ዓ/ም የተመሰረተው ባታ ጫማ በአምስት አህጉር ከ70 በላይ ሀገሮች ላይ 5300 የጫማ መደብሮች ያለው ሲሆን በ21 ሀገሮች ላይም የጫማ ማምረቻ አሉት በችርቻሮ መደብሮቹም ለድንበኞቹ በሁሉም የእድሜ ክልል ላሎ ወንድና ሴቶች እንዲሁም ህፃናት የተለያዪ አይነት የጫማ አማራጮች ይዞ የድንበኞቹን ፍላጎት በማርካት ላይ ይገኛል ።
ፒላርሰ ትሬዲንግ በአጭር ጊዜ እቅድ ምርቶችን በማስመጣት ለገበያ ለማቅረብ ቅድመ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን በቀጣይ 5 አመታት ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ 100 ያህል የመሸጫ ሱቆችን የመክፈት እቅድ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ሲሆን የመጀመሪያው ሱቅ ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት የሺ ህንፃ ግራውንድ ላይ በቅርቡ ከፍቶ ስራውን ይጀመራል። ከዚህም ጎን ለጎን በቀጣይ ሁለት አመታት ውስጥ በሀገር ውሰጥ የጫማ ምርት ለመጀመር እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑን ይገልፃል ።
እነዚህኑ ምርቶች በመሸጥ እና በማከፋፈል ከድርጅታችን ጋር መስረት ለሚፈልጉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ልዩ ዕድል የተመቻቸ መሆኑ ተገልጿል ።


