banner

#የሞቱት አሕዮች ጭንቅላት ተቀያይሮ ቢገጠምም…

በቅድስት ቤተ ክርስቲያችን ትልቅ ስራ ከሰሩና ትልቅ ተጋድሎ ካላቸው ቅዱሳን አባቶች አንዱ ቅዱስ ቶማስ ዘመራስ ነው፡፡ መራስ የትውልድ ሀገሩ ናትና በዚያው ይጠራል፡፡ ዲዮቅልጥያኖስና መክስሚያኖስ በክርስቲያኖች ላይ መከራ ባጸኑበት ዘመን ለ22 ዓመታት የተጋደለው ይህ ድንቅ ሰማዕትና ሐዋርያ ገና በወጣትነቱ መንኖ ገዳም የኖረ፣ በጾም፣ በጸሎት፣ በሰጊድ፣ ቀንና ሌሊትም በመትጋት ለድኆችና ለምስኪኖችም በመራራት ተጠምዶ የኖረ ነበር፡፡

በጨካኞቹ ነገስታት ዘመንም ለጣኦት እንዲሰግድ የደረሰበትን መከራ ታግሶ በክርስቶስ ፍቅር በመጽናቱ በ22 ዓመታት የመከራ ጊዜው ጨለማ ውስጥ ጥለውት አካሉን እየቆራረጡ ለጣዖታቸው ያጥኑ ስለነበር 2 እግሮቹ፣ 2 እጆቹ፣ 2 ጀሮዎቹ፣ አፍንጫውና ፪ ዐይኖቹ አልነበሩም፡፡ የተጣለበትን ስፍራ የምታውቅ አንዲት ሴትም በስውር እየገባች ትመግበው ነበር፡፡

እኛ በዘመናችን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፍቅር የትኛውን አካላችን እንድንሰዋ አልጠተየቅንም፤ ወይም በረሀብ አልተቀጣንም፡፡ ይልቁንም በነጻነት የምናመልክበት እድል እነዚህ ቅዱሳን አባቶቻችን መከራውን ታግሰው ባቆዩልን እምነት መጽናትና ቤተ ክርስቲያናችንን በተሰጠን ስጋዊና መንፈሳዊ ሃብት ማገዝ ብቻ ነው የሚጠበቅብን፡፡

የቤተክርስቲያን የመከራ ዘመን አልፎ ንጉስ ቆስጠንጢኖስ ስልጣን ከተረከበ በኋላ በኒቂያ ጉባኤ አርዮስን ለማውገዝ ከተሰበሰቡት 318 ሊቃውንት አንዱ ቅዱስ ቶማስ ዘመራስ ነበር፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ስጋዊ አካሉ የጎደለውን ቅዱስ ሰማዕት በቅርጫት አድርገው በአሕዮች ጭነው ለቀናት ተጉዘው ነበር ወደ ኒቂያ የወሰዱት፡፡ በመንገድ ላይ ሳሉም ካደሩበት ቦታ የአርዮስ ተከታዮች የአሕዮቹን ራስ ቆርጠው ገድለዋቸው ሔዱ፡፡

ምንም እንኳን ሁለት አይኖቹ ቢጠፉም መንፈሳዊ ምጥቀቱ ከፍ ያለ ነበርና በሌሊት ገስግሰው ሊጓዙ ሲነሱ የአሕዮቹን ሁኔታ ደቀ መዛሙርቱ ሲነግሩት ቀድሞ አውቆት ነበርና ጭንቅላታቸውን ከአካላቸው ጋር እንዲገጥሙት አዘዛቸው፡፡ ከዚያም ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት አሕዮቹ እደገና ነፍስ ዘርተው ተነስተው መንገዳቸውን ቀጥለዋል፡፡ አስገራሚው ነገር በጨለማው ምክንያት አንዱን ከአንዱ መለየት ስላልቻሉ የነጩን አሕያ ጭንቅላት ለጥቁሩ፣ የጥቁሩንም ለነጩ እንደገጠሙላቸው ጠዋት በብርሃን አዩት፡፡

ቅዱስ ቶማስ ዘመራስም አርዮስን አውግዞ ወደ ሀገሩ ስብከቱ ተመልሶ ጸሎተ ሃይማኖት የተባለውን ጸሎት ለሕዝቡ አስተምሯል፡፡ በተጨማሪም ለ40 ዓመታት በጵጵስና አገልግሎ አልፏል፡፡ ቅዱሳን አባቶች በትልቅ መስዋዕትነት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተው ያቆዩዋትን እምነት ለመጠበቅ እጃችንን እንድንዘረጋ መጠየቅ በራሱ ከበረከታቸው መካፈል ነውና ገዳማትን እንርዳ፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

1 comment

Sibira Sinmone November 22, 2024 - 5:00 am

Dedeboch

Reply

Leave a Comment