banner

ለአክሱም ፅዮን ማርያም ክብረ በዓል 1 ሚሊዮን የሚጠጉ እንግዶች እንደሚገኙ ይጠበቃል ተባለ

የአክሱም ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገብረ መድህን ፍፁም ብርሀን ለዓመታዊው የአክሱም ጽዮን ማርያም ክብረ በዓል 1 ሚሊዮን የሚጠጉ እንግዶች እንዲሚጠበቁ ተናግረዋል።

የቱሪዝም ፅ/ ቤቱ እንደገለፀው በህዳር 21 በሚከበረው የንግስ በአል ላይ 5 ሚሊዮን ብር ገቢ ይገኛል የሚል ዕቅድ መያዙን ገልጿል።

ቢሮው የከተማውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ከሚደግፉ ነገሮች አንዱ የአክሱም ፂዮን የንግስ በአል እንደሆነ ገልፆ በዚህም የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙም አንስቷል።

ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ ተቀዛቅዞ የነበረውን የከተማዋን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለመመለስ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

የአየር መንገዱም እድሳት ትልቅ ግብአት እንደሆነም ተመላክቷል ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ነው የዘገበው።



1 comment

Muler Social Media Marketing November 25, 2024 - 8:40 am

ዘንድሮም ቁጥር አይፈሩም😂

Reply

Leave a Comment