0
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን የቀድሞ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሀላፊ የነበሩት አቶ ጥላሁን ሞላ ሥልጣንን ያለ አግባብ በመጠቀም ወንጀል ተጠርጥረዉ በህግ ጥላ ስር ውለው በፖሊስ ምርመራ እየተጣራባቸዉ ካለበት ፖሊስ ጣቢያ ማምለጣቸው ተገለጸ፡፡
አቶ ጥላሁን ሞላ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩበት ከሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ ከእስረኛ ማቆያ ህዳር 08 ቀን 2017 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 2 ሰዓት አከባቢ አምልጠው መጥፋታቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
በእለቱ የጥበቃ ተረኛ ፖሊስ አባሎችም በቁጥጥር ስር በማድረግ በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል ብሏል።
የሀዲያ ዞን ፖሊስ አዛዥ ዋ/ኢ/ር ተሾመ ባቲሶ ማንም ከህግ የሚያመልጥ እንደሌለ በመግለጽ ጥፋተኛ እና በወንጀል የሚጠረጠር ሁሉ በህግ እንዲጠየቅ ለማድረግ ፖሊስ ብርቱ ክትትል ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የተጠርጣሪውን ለመያዝ ፖሊስ የቅርብ የሚባሉ ሰዎችንም እየመረመረ እንደሚገኝና እስካሁን ግን ምንም የተገኘ ፍንጭ እንደሌለም ተገልጿል።
ዘገባው የአዲስ ስታንዳርድ ነው።

10 comments
Mr. Prison Break!
ዘመኑ ተፈፅሟል ኢየሱስ ልመጣ በደጅ ነው ለሰው ልጅ የተሰጠው ብቻኛ መዳኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው እርሱ ከሁሉም ነገር በፍት ነበረ ዘመኑ በደረሰ ግዜ ከሴት ተወልዶ እኛን በደሙ ለማዳን ሕይወቱን ሰጠን ኢየሱስ ይወዳችኋል ❤️💙💚💛
ቁልፍ ገዝተው ነው ❓
ይመቸው 👏
Prison break በኢትዮጲያ
አታስቡ ደቡብ አፍሪካ በሰላም ደርስዋል😂
ዘገባህን አስተካክል አንተ ከማረሚያ ሳይሆን ከፖሊስ ጣብያ ነው።
እናንተ እራሱ ሌባ ናቹ ፎቶው ለምን አትለጥፉም
ይሄኔ ደቡብ አፍሪካ ገብቷል 😄
እና በፊት የዘረፍት ብር እንኳን ከእስር ከሞትም ያስመልጣል፡፡