0
በሀዋሳ ታቦር ክፍለ ከተማ ቱሩፋት ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የሞተር ሳይክል የሰረቁ ተጠርጣሪዎችን በ CCTV (የደህንነት ካሜራ) በመታገዝ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ ተጠቆመ።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልል የፀጥታ ተቋማት በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች መደራጀት ለክልሉ ፀጥታ ግብረ-ሃይል የወንጀል ክስተቶችን አስቀድሞ ለመከላከልና ወንጀል ፈጽመው የሚሰወሩ ተጠርጣሪዎችን በህግ ጥላ ስር ለማዋል አቅም የፈጠረ እንደሆነ ግብረ ሃይሉ አስታውቋል።
የፀጥታ ግብረ-ሃይሉ እንደገለፀው ከሁለት ወር በፊት በታቦር ክፍለ ከተማ ትሩፋት አካባቢ ሞተር ሳይክል ሰርቀው ያመለጡ 2 ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል ሲያደርግ እንደነበርና በዛሬው ዕለት በ Face recognition AI CCTV በመታገዝ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን አስታውቋል።




3 comments
ዋው ትልቅ ኦፕሬሽን😁😁😁
ከእነርሱ ይልቅ እናንተ ተካፋዮች ነው የገረማቹኝ 😁
ሀዋሳ ወይ ሲዳማ ፍቅርና ሰላም ተምሳሌት ናት 🇬🇲
Nice security force🙏