banner

ዘማሪ ዲ/ን በርሱፈቃድ አንዳርጋቸው ሁለት አልበሞችን በአንድ ቀን ሊያስመርቅ ነው

#FastMereja I ዘማሪ ዲ/ን በርሱፈቃድ አንዳርጋቸው ሁለት አልበሞችን የፊታችን ታኅሣሥ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በቦሌ ደብረ ሳሌም ትልቁ አዳራሽ እንደሚያስመርቅ በዛሬው ዕለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

ከዐሥራ ዐራት ዓመታት በኋላ የተሰሩት እነዚህ ሁለት ዝማሬዎች ቁጥር ስድስት አልበሙ ሁሉ በእርሱ ፈቃድ የሚል መጠሪያ ሲኖረው፤ ቁጥር ሰባት አልበሙ ወዳሴ ማርያም ጩኽቴ ይሰኛሉ።

ቁጥር ስድስት አልበሙ ሁሉ በእርሱ ፈቃድ የሚለውን ጨምሮ በድምሩ 16 መዝሙራትን የያዘ ሲሆን የሚያየኝን ጌታየን አየሁት፣ ኪዳነ ምሕረት፣ ቆሞ የሔደ ሰው ፣ የመላእክት እሕት፣ እመ ብርሃ እምዬ፣ በቅዱሳኑ ላይ፣ አንዴ ለቅዱሳን፣ ዐይኔ አማተረ፣ መልአከ ሩፋኤል እለዋለሁ፣ ማር ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሰምህ ሲጠራ፣ ከአርያም ሰማይ ላይ፣ ኢትዮጵያ ቃተተች፣ የተወልኝ ብዙ እና ስደቱ ታከተኝ ተካተውበታል፡፡ ቁጥር ሰባት አልበሙ ደሞ ውዳሴ ማርያም ጩኸቴን አካትቶ ዘሰኑይ፣ ዘሥሉስ፣ ዘረቡዕ፣ ዘሐሙስ፣ ዘዓርብ፣ ዘቀዳሚት፣ ዘእሑድ፣ አንቀጸ ብርሃን፣ ይዌድስዋ መላእክት የተሰኙ ሲሆን በእነዚህ በርካታ ዝማሬዎች ላይ ልዩ ልዩ ጸጋ ያለቸው ገጣሚያን፣ የዜማ ደራሲያን፣ የዜማ መሣርያ ተጫዎቾች እና አቀናባሪዎች ደክመውበታል ተብሏል።

ዘማሪ ዲ/ን በርሱ ፈቃድ አንዳርጋቸው ከዚህ በፊት በዜማ እና ግጥም ከደረሳቸው ዝማሬዎች መሀከልም
ኑና ማርያምን እናመስግናት፤ ግጥም እና ዜማ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ራሷ ሀገር ናት፤ ግጥም እና ዜማ
ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ፤ ግጥም እና ዜማ
ይቅርታ ነው ተስፋዬ፤ ግጥም እና ዜማ
ማርያም ማርያም ነው ዝማሬዬ፤ ግጥም እና ዜማ
ከአዲሲቹ ሁለት አልበሞቹ ውስጥም በዜማ እና ግጥም ድርሰት ላይ የነበረው ተሳትፎ ቀላል እንዳልነበር ተገልጿል።





2 comments

እድል አበራ December 5, 2024 - 11:12 am

❤❤❤❤

Reply
Seni Seni December 5, 2024 - 11:16 am

🙏🙏🙏

Reply

Leave a Comment