banner

በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ ሿሿ የተባለውን ወንጀል የፈፀሙት 3 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ

በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ ሿሿ የተባለውን ወንጀል የፈፀሙት 3 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ቂሊንጦ አካባቢ ነው። በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ቂሊንጦ አካባቢ የተጠርጣሪዎቹ መነሻ ቦታ ሲሆን ኮድ2,A,62663አ.አ ቪትስ ተሽከርካሪ በመያዝ አንድን ግለሰብ መንገድ ስለጠፋብን አሳየን በማለት ወደ ተሽከርካሪያቸው ካስገቡትና 100 ሜትር ያህል ከተጓዙ በኋላ መንገዱን አግኝተነዋል ብለው ከተሽከርካሪው ያስወርዱታል።

የግል ተበዳይም ከወረደ በኋላ ስልኩ እንደተወሰደበት ወዲያው በማረጋገጡ ስልኬን ሰርቀውኝ ነው ያዙልኝ እያለና እየጮኸ ይከተላቸዋል። የግለሰቡን የድረሱልኝ ጥሪ የሰሙ በአካባቢው ላይ የነበሩ ግለሰቦች በተሽከርካሪያቸው ሳሪስ አቦ አካባቢ ድረሰ ተከታትለው በአካባቢው ላገኟቸው ፖሊሶች ጉዳዩን አስረድተው ፖሊስ ተከታትሎ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ውሃ ጋን አካባቢ ሦስቱንም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።

ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በተገኘው መረጃ መሠረት ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ተሽከርካሪው ሲፈተሽ የግለ ተበዳይ ተሰረቅኩ ያለው ስልክ መገኘቱን ያስታወቀው ፖሊስ በኮድ2,A,62663 አ.አ ቪትስ በሆነ ተሽከርካሪ እና በነዚህ ሦስት ተጠርጣሪዎች ወንጀል ተፈፅሞብኛል የሚል ማነኛውም ግለሰብ ወደ ፖሊስ ቀርቦ ማመልከት ይችላል ብሏል።

ህብረተሰቡም በመሰል የወንጀል ድርጊት ሰለባ እንዳይሆን ጥንቃቄ ከማድረጉም ባሻገር ፈፃሚዎችን ሲመለከት ለሚመለከተው የፀጥታ አካል መጠቆም ይኖርበታልም ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ አሳስቧል።

1 comment

Alelign Tegbu December 7, 2024 - 7:14 am

ስልኬን የበሉኝ🙄

Reply

Leave a Comment