banner

ኢትዮ-ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር የአፍሪካ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ቀንን አከበረ

ሆስፒታሉ ህዳር 27/2017 ዓ.ም የተከበረውን ‘የአፍሪካ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ቀን’ ከአፍሪካ ህብረት ጋር አንድ ላይ በመሆን ነፃ የጤና ምርመራ እና ምክር አገልግሎት በመስጠት አክብሮ ውሏል።

በተጨማሪም ሆስፒታሉ ከአፍሪካ ኀብረት ጋር የሕክምና አገልግሎት ስምምነት ፈፅሟል። በዚህ ስምምነት የድርጅቱ ሰራተኞች በሆስፒታሉ ሕክምና አገልግሎት ያገኛሉ።

ኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል በቴክኖሎጂ በታገዘ የአገልግሎት አሰጣጡ፣ ማኀበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየተጋ የሚገኝ ተቋም ነው።





Leave a Comment