ከ130ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት እና የቤት ስጦታ ሽልማት የሚያሰጠዉ ኤክስፖ የፊታችን ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ይከፈታል።
ከ400 በላይ ድርጅቶች የሚካፈሉበት የአዲስ ገና 2017 ኤክስፖ ከታህሳስ 4 ቀን እሰከ ታህሰሳስ 28 ቀን 2017 ዓ.ም በኤግዢቢሽን ማዕከልና በመስቀል አደባባይ በድምቀት ይከፈታል።
አዲስ ገና 2017 ኤክስፖ ሮበስት ቢዝነስ ግሩፕና ሰላሳ መልቲሚዲያ በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር በጥምረት እየሰራ ይገኛል ተብሏል።
ሁለቱ ተቋማት በተመሳሳይ ዝግጅቶች ከፍተኛውን የጨረታ ዋጋ በመክፈል አዲስ ገና 2017 ዓ.ም ኤክስፖ ለተከታታይ 25 ቀናት ለመጀመርያ ጊዜ በመስቀል አደባባይ እና በኤግዚቢሽን ማዕከል የሚደረግ ይሆናል።
ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ጎብኚዎች ይጎበኙታል ተብሎ የሚጠበቀው አዲስ ገና 2017 ዓ.ም ኤክስፖ ከ100 በላይ የሙዚቃ ሰዎች ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በዘንድሮ ኤክስፖ ላይ በሀገሪቱ የሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት የሸማች ማህበራት የሪልዕስቴት ተቋማትና የመኪና አስመጪዎች ይገኛሉም ተብሏል።
ለህበረተሰቡ በአነስተኛ ዋጋ ምርቶችን የሚያቀርቡት ቀጥተኛ አምራቾች የንግድ ወኪሎች አገልግሎት ሰጪዎችና ሌሎችም ተቋማቶች እንደሚሳተፉ ነው የተገለጸው።
በአዲስ ገና 2017 ዓ.ም ኤክስፖ ለመደመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ የኤግዚቢሽን ታሪክ በቴሌብር የመግብያ ደረሰኝ የሚቆርጡና በቴሌብር የሚገበያዩ ጎብኚዎች የቤት ሽልማት መዘጋጀቱን ተነግሯል።
ኤክስፖው ለተከታታይ 25 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በቆይታውም እረጅም ቀናቶች የሚቆይ ኤክስፖ ነው ተብሏል።
ጎብኚዎች ኤክስፖውን ለመሳተፍ 100ብር ብቻ በመክፈል መሳተፍ ይችላሉ ተብሏል።የቤት ሽልማት ይዞ የመጣው የገና ባዛር ከታህሳስ 4 ቀን ጀምሮ ይከፈታል ተባለ።
ለ 25 ቀናት የሚቆየው አዲስ ገና 2017 ኤክስፖ በዚህ ሳምንት መጨረሻ እንደሚከፈት ሰምተናል።
በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል እና በመስቀል አደባባይ የሚካሄደው ይህ ባዛር ከ500 አምስት መቶ በላይ ነጋዴዎች ምርታቸውን የሚያቀርቡበት ነው ተብሏል።
በዚህ ባዛር ላይ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሸማቾች እና ጎብኚዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ከአዘጋጆቹ ሰምተናል።
የተጋነነውን የዋጋ ንረትን ለማስቀረት ሸማቹ ምርቱን ቀጥታ ከአምራች እና አስመጪዎች ላይ የሚገበያይ ይሆናል ተብሏል።
ሸማቹ ለበዓል ብቻ ሳይሆን በየዕለቱ የሚጠቀማቸውን እንደ ስኳር፣ ሩዝ፣ ዱቄት እና ዘይት ያሉ የምግብ ግብዓቶችን በፋብሪካ ዋጋ ትራንስፖርት ጨምሮ መግዛት ይችላል ነው የተባለው።
የባዛሩ መግቢያ ከ1መቶ ብር እስከ 2መቶ ብር ድረስ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ የመጀመሪያዎቹን ቀናት በመቶ ብር የበዓሉ ወቅት ሲቃረብ ያሉትን ቀናት ደግሞ በ2 መቶ ብር በመግባት መገበያየት ይችላሉ ተብሏል።
በተጨማሪም የባዛሩ መጠናቀቂያ ዕለት በሚወጣ ዕጣ ሸማቾች የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ጋር በዕጣ አወጣጡ ዙሪያ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።
ይህን ኤግዚቢሽን እና ባዛር ሮበስት ቢዝነስ ግሩፕ እና ሠላሳ መልቲሚዲያ በጋራ አዘጋጅተውታል።




