banner

ከደቡብ ሱዳን ተነስተዉ በሱሪ ወረዳ ከብት ለመዝረፍ የሞከሩ አርብቶ አደሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ከደቡብ ሱዳን መነሻቸዉን አድርገዉ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሚገኘዉ ምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ የአርብቶ አደሮችን ከብቶችን ዘርፈዉ ለመሄድ የሞከሩ 46 የደቡብ ሱዳን አርብቶ አደሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ

የኢፌዲሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣የፌዴራል ፖሊስ እና የክልልና የአካባቢዉ ፖሊስ በመቀናጀት በቁጥጥር ስር ማዋላቸዉን የክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ገልጸዋል::

የተዘረፉ 250 ከብቶች እና 21 የተለያዩ ጦር መሳሪያዎች መያዛቸዉን ኃላፊዉ አመልክተዋል።

የተመለሱ ከብቶች ለባለቤቶች የተሰጡ ሲሆን ዘራፊዎቹ በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ አቶ አንድነት አሸናፊ ገልጸዋል ሲል የክልሉ መንግስት ኮሚንኬሽን ዘግቧል።



3 comments

መስፍን ተስፋዬ December 13, 2024 - 2:18 pm

ዘርፈውም አርብቶ አደሮች ብሎ መጥራት ምን ማለት ነው

Reply
ተመስገን ማከይ December 13, 2024 - 2:19 pm

እናመሰግናለን በርቱልን🙏

Reply
Adamu Tulu December 13, 2024 - 2:21 pm

Bedenb yegerfu 40 40 cherashe ensum nekwenal / tedfaferen

Reply

Leave a Comment