
በቤተ ክርስቲያናችን አበይት ነቢያት ለሚባሉት አንዱ ቅዱስ ኢሳይያስ ነው፡፡ በዘመኑ የነበረው ንጉስ ዖዝያን ኃጢአት ሲሰራ እያው ዝም አለው፡፡ በዚህም ምክንያት ከንፈሩ በለምጽ ተመታ፡፡ በኋላም ንጉሱ በሞተበት ዓመት “ቅዱስ እግዚአብሔር ከፍ ባለና ልዕልና ባለው ዙፋን ላይ ተቀምጦ መጐናጸፊያውም ቤተ መቅደሱን ሞልቶት” ለነቢዩ ታየው፡፡ አንተ ትፈራው የነበረው ንጉስ ሞተ እኔ ግን ሕያው ነኝ ሲል፡፡ እርሱም ይሕን በማየቱ ፈርቶ የሚሞት መስሎት ወዮልኝ አለ፡፡
እኛ ግን ድንቅ ምስጢር በሚፈጸምባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በደስታ ገብተን ጸጋውን ተቀብለን ሕይወትም አግኝተን በሰላም እንወጣለን፡፡
ነቢዩ ስለዚህ ነገር በትንቢተ ኢሳያስ 6፣1-7 ሲናገር “ከእነዚያም መላእክት አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፤ ከመሠዊያው የወሰደው የእሳት ፍም የያዘበት ጒጠት በእጁ ነበር። በእሳቱም ፍም ከንፈሮቼን ነክቶ እነሆ ይህ የእሳት ፍም ከንፈሮችህን ስለ ነካ በደልህ ተወግዶልሃል፤ ኃጢአትህም ይቅር ተብሎልሃል አለኝ።” ይላል፡፡
የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባቶችም መልአኩ በጉጠት የያዘው ፍም የቅዱስ ስጋውና የደሙ ምሳሌ ነው ይሉናል፡፡ መልአኩ ስልጣነ ክህነት ስለሌለው በጉጠት የያዘውን እሳት ካሕናት አባቶች ዛሬ በእጃቸው ፈትተው ያቆርቡናል፡፡ የካሕናት ስልጣን ትልቅ ነው፡፡
ታዲያ ይህን መንፈሳዊ ስራ የሚያከናውኑባት ቤተ ክርስቲያን ደሳሳ ጎጆ ሆና፣ ዝናብ እያፈሰሰች ዝም ማለት እንደምን ይቻለናል???
በማዕከላዊ ጎንደር ምስራቅ በለሳ ወረዳ ለሚገኘው ሙት አንሳ ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ለሚገኙ መነኮሳት እጃችንን እንዘርጋ፡፡
ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለተጨማሪ መረጃ:-
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957
ወይም 0938644444