banner

የቴክኒክ ችግር ያጋጠመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በሰላም ማረፉ ተገለጸ

የበረራ ቁጥሩ ET 612 የሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የቴክኒክ ችግር ስላጋጠመው ተመልሶ በሰላም ማረፉን አየር መንገዱ አስታወቀ።

ትናንት ታህሳስ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ በሚያደርገው በረራ ከተነሳ ከ30 ደቂቃ በኋላ የቴክኒክ ችግር ስላጋጠመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሰላም አርፏል።

ለጥንቃቄ ሲባል መንገዶች እና የበረራ ሠራተኞች በአስቸኳይ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ መደረጉም ተገልጿል።

ዘወትር ለመንገደኞቹ ደህንነት ቅድሚያ እንደሚሰጥ የገለጸው አየር መንገዱ፤ መንገደኞች ለደረሰባቸው መጉላላት አየር ይቅርታ ጠይቋል።

የቴክኒክ ችግሩ በመጣራት ላይ እንደሆነም አመልክቷል።

4 comments

Henok Assefa December 15, 2024 - 4:47 am

Wanew be selam memelesachew nw

Reply
Abel Dereje December 15, 2024 - 4:47 am

ተመስገን

Reply
Addunyaa Dhufeeraa December 15, 2024 - 4:51 am

Abiy Amhed namoota achi keessa hojjetan hunda hanga hin ariinetti jijjiiramni tokkollee hin jiru.

Reply
Hadero Abate December 15, 2024 - 4:52 am

ምነው ኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ መደጋገም አበዛ ፣ ዘላቂ መፍትሔ የሚፈልጉ ነገሮች በጣም እየተበራከቱ ነው።

Reply

Leave a Comment