banner

Public Speaking (የተሰበሰቡ ሰዎች ፊት ንግግር ማድረግ)

በፍፁም አጥናፈወርቅ

ንግግር ትልቅ ችሎታ (skill) ነው። መሰልጠን እና መለማመድ ይፈልጋል። የንግግር ዋና አላማዎች መልእክት ለመስጠት፣ ለማነቃቃት፣ ለማስተማር፣ ለማዝናናት፣ ለመተረክ ነው፣ ከእነዚህ አያልፍም። ግን ጥሩ ተናጋሪ ካልሆንን አላማችን ኢላማውን አይመታም። ብዙዎቻችን የንግግር ችሎታ ትልቁ ቻሌንጃችን ነው። እንቸገራለን፣ እንፈራለን፣ እንንቀጠቀጣለን፣ ሀሳባችን ይጠፋብናል፣ ነርቨስ እንሆናለን፣ ወዘተ።

ፐብሊክ ስፒኪንግ ለንግድ ስራ፣ ለቢሮ ስራ፣ ለስልጠና እና የማማከር ስራ፣ ለስብከት ስራ፣ በአጠቃላይ ለሁሉም ግንኙነት (communication) አስፈላጊ ነው። ሁላችንም መለማመድ እና ማሻሻል አለብን። እንዴት ለሚለው የሚጠቅሙን ነጥቦች እነሆ:-

1ኛ. የምንናገርበት ርእሰጉዳይ በደንብ እንዘጋጅበት፣ በመረጃ እና በምሳሌ ጽፈን አደራጅተን፣ መግቢያ አተታ እና መዝግያ አበጅተን (ብትንትን እንዳይልብን) ተጠንቅቀን ከዚያም ተለማምደን መቅረብ አለብን።

2ኛ. ንግግራችንን የምናቀርበው ለማነው? ለኃላፊዎች/መሪዎች? ለምርትና አገልግሎታችን ተጠቃሚዎች? ለወጣቶች? ለጓደኞች? ለሕጻናት? ወዘተ ለይተን እንወቅ። መልእክቱ በአድማጮቻችን (Audiences) ልክ የተሰፋ (የተሰደረ) መሆን አለበት።

3ኛ. እራሳችንን እንሁኑ! ለንግግር ብለን ማንነታችንን አንቀይር። በእራስ መተማመን (self confidence ) ይኑረን። አለበለዝያ የማስመሰሉ ሂደት (ድራማው) ትኩረታችንን ይስበውና መልእክታችን ግቡን ሳይመታ ይቀራል።

4ኛ. ንግግራችንን ደረቅ አናድርገው። ስሜት እንዝራበት። ትረካ፣ ቀልድ፣ ፈገግታ ማከል ከቻልን አድማጮቻችን አይሰላቹም። በተለይ ከበድ ያሉ ምሳሌዎችን በቀልድ፣ በምሳሌ እና ትረካ (story telling)መስጠት ከቻልን አይረሱትም፤ ይደመጥልናልም።

5ኛ. የሰውነት እንቅስቃሴ ላይ ልምምድ እናድርግ። ግትር ብለን፣ አንድ ሰው ላይ አተኩረን ወይንም በመስኮት ወደውጪ እያየን አልያም እጃችንን ኪሳችን ከተን ወይም አጣምረን፣ መሬት መሬት፣ ጣራ ጣራ እያየን የምናወራ ከሆነ መልእክት አዲዮስ፣ ከአድማጭ ተለያይተናል። በጣም የምንወራጭም ከሆነ እንደዚያው።
ስለዚህ አይናችን ከአድማጮቻችን ጋር መቃኘት፣ የሰውነት እንቅስቃሴአችን የማይረብሽ ሆኖ መልእክቱን የሚያግዝ መሆን አለበት።

6ኛ. አለባበሳችን ጥሩ ይሁን! አድማጮች ማክበርያ አንዱ አለባበስ ነውና። በጣም ማጌጥም የለብንም፣ መዝረክረክም የለብንም። ቀለል ያለ ሆኖ የሰውነት እንቅስቃሴአችንን የማያግድ፣ ያልተገላለጠ፣ ያልተጠባበቀ፣ መድረክ ከሆነ ስፖርታዊ ያልሆነወዘተ።

7ኛ. Practice does not make it perfect! እኛም አላማችን ፐርፌክት መሆን የለበትም። በንግግር ፐርፌክሽን በእኛ ደረጃ ቀርቶ የትም የሚታሰብ አይደለም። አላማችን ነርቨስ መሆናችንን ተቆጣጥረን ከቀድሞ የተሻለ ተደማጭ አላማውን እና ግቡን የሚመታ ንግግር ማድረግ ነው። ለዚህ ልምምድ እናድርግ።

8ኛ. ጊዜና አቅም ሲፈቅድላችሁ ቶስትማስተርስ ክለብ ሂዱ እና መሠረታዊ ክእሎቶችን ተለማመዱ።

9ኛ. በሰዓት መገኘት ጥሩ ነው። ሀሳብና ቀልብን ሰብሰብ አድርጎ፣ በቂ አየር ተንፍሶ መድረክ መረከብ ይቻል ዘንድ።

10ኛ. ከሌሎች ተናጋሪዎች ጋር (ካሉ) እራሳችንን አወዳድረን አናሳንስ። እኛ እኛ ነን። ከእከሌ በኋላ መናገር ምናምን አንበል። ነርቨስ ያደርገናል፣ አድማጮችም አነስ እንዲያደርጉን signal እየሰጠን ነው። በራሳችን እንተማመን!

በነገራችን ላይ የእኔ ንግግር የሚመስጣችሁ ካላችሁ በቶስት ማስተርስ ክለብ የታገዘ ነው። እንደዚያም ሆኖ ንግግር አድጎ ስለማያልቅ ሁልጊዜ ልምምድ፣ ይፈልጋል። አሁን ወደ ክለባችን ስለማልሄድ ፐብሊክ ስፒቾችን ከ TEDX እና ሌሎችም ቻነሎች አያለሁ፣ አዳምጣለሁ።

ከቻላችሁ ግን አንዱን ክለብ ተቀላቅላችሁ ተለማመዱ። አሪፍ ተናጋሪዎችና አድማጮች ይብዙልን!

5 comments

Ezedin Sultan December 17, 2024 - 8:22 am

Fitsum Atnafework Kidanemariam

Reply
Bereket Mognhode December 17, 2024 - 8:28 am

🌸:አያቴ ነብሱን ይማረው እና ምን ይለኝ ነበረ መሰላችሁ “አንድ ቀን የሚሰሩትን ስራ ትተው facebook ላይ ያንተን የማይረባ ኮመንት በማንበብ ጊዜያቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ይመጣሉ” ይለኝ ነበር።

Reply
የቲ ሰለሞን December 17, 2024 - 8:28 am

Fitsum Atnafework Kidanemariam

Reply
Mohe Muste December 17, 2024 - 8:28 am

ምርጥ ምክር ነው!!

Reply
Biruk CR December 17, 2024 - 8:29 am

What’s funny about this post ቆይ??😂

Reply

Leave a Comment