0
#FastMereja I ። ቴሌብር አዲስ ገና 2017 ኤክስፖ የከፈቱት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚንስትር ካሳሁን ጎፌ (ፒኤችዲ) ሲሆኑ ከ400 በላይ ድርጅቶች የሚካፈሉበት ቴሌብር አዲስ ገና 2017 ኤክስፖ በኤግዚቢሽን ማዕከልና በመስቀል አደባባይ እሰከ ታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።
ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ጎብኚዎች ይጎበኙታል ተብሎ የሚጠበቀው አዲስ ገና 2017 ዓ.ም ኤክስፖ ከ100 በላይ የሙዚቃ ሰዎች ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ቴሌብር አዲስ ገና 2017 ኤክስፖ ሮበስት ቢዝነስ ግሩፕና ሰላሳ መልቲሚዲያ በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር በጥምረት ይሰራል ተብሏል።
ቴሌብር አዲስ ገና 2017 ዓ.ም ኤክስፖ ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ የኤግዚቢሽን ታሪክ በቴሌብር የመግቢያ ደረሰኝ የሚቆርጡና በቴሌብር የሚገበያዩ ጎብኚዎች የቤት ሽልማት መዘጋጀቱን ተነግሯል።




