banner

የአሥራ አንድ ዓመት ሕፃን ልጅ በማገት 4 ሚሊዮን ብር የጠየቀው በቁጥጥር ሥር ዋለ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ የአስራ አንድ ዓመት ሕፃን ልጅ በማገት ወደ ሸገር ከተማ በማምጣት 4 ሚሊዮን ብር የጠየቀውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር አውሏል።

አጋች አበራ አላዩ ቸርነት ህዳር 21 ቀን 2017 ዓም ከምሽቱ 4:30 ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ የሚገኘውን የአቶ አውሌ ገብሩ ሀብተሚካኤል መኖሪያ ቤትን ሰብረው በመግባት በጥይት በማስፈራራት ሕፃን ባሳዝነው አውሌ ገብሩን አግተው ለሦስት ቀናት ዋሻ ውስጥ በማሳደር ሕፃኑን ይዘው በእግር እስከ ፍቼ ከተጓዙ በኋላ ሁለተኛው አጋች ገብረመድን አላዩ ቸርነት ወደ አማራ ክልል ተመልሷል፡፡

አጋቹ አበራ አላዩ ለሕፃኑ አባት ለአቶ አውሌ ገብሩ ሀብተሚካኤል ስልክ በመደወል 4 ሚሊዮን ብር እንዲከፍል ይህ ካልሆነ ግን ሕፃኑን በሕይወት እንደማያገኘው በማስፈራራት ላይ እንዳለ ጉዳዩን የሰማው አዲስ አበባ የሚኖረው የሕፃኑ አጎት ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ EFPApp ሞባይል መተግበሪያ ያደረሰውን መረጃ መነሻ በማድረግ በተከራየው መኖሪያ ቤት ውስጥ ከተባባሪ ባለቤቱ ጋር እጅ ከፍንጅ በመያዝ በቁጥጥር ስር አውሎ የሕፃኑን ሕይወት መታደግ መቻሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል፡፡

6 comments

ቲጂ የመይሳው ልጅ December 17, 2024 - 3:16 pm

ከወንዱ የሴቲቱ ጭካኔ😭

Reply
Medina Ya Emaye Lij December 17, 2024 - 3:16 pm

ውርድታም

Reply
Natty Drogba December 17, 2024 - 3:18 pm

ቁጥር አይፈሩም 😂😂😂😂

Reply
Seyfe Semae December 17, 2024 - 3:19 pm

አይ ሀበሻ በፊልም ያየውን ሁላ
በተግባር ያሳዝናል

Reply
Ame Ase December 17, 2024 - 3:21 pm

Ye11 amet hitsan yet nech tadiya

Reply
Keka Gezahegn December 17, 2024 - 3:25 pm

4 ሚልየን 😏😏😏

Reply

Leave a Comment