እናት ባንክ “የዓመቱ ድንቅ እናት” የተሰኘ ውድድርን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሁም “ለእናቴ” የተሰኘ ሀገራዊ የጽሑፍ ውድድርን ለሁለተኛ ጊዜ ማወዳደሩን በይፋ ጀመረ!
ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው “የዓመቱ የእናት ባንክ ድንቅ እናት” የተሰኘው ውድድር፣ ተወዳዳሪዎች በአካባቢያቸው የሚያውቋቸውን ወይም የራሳቸውን እናቶች፣ በድምጽና በምስል ቀርጸው በቀጥታ በመጠቆም የሚሳተፉበት ውድድር ነው፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ የሚደረገው “ለእናቴ” የተሰኘ የጽሑፍ ውድድር ደግሞ፣ በዋናነት ሁሉም ሰው ለእናቱ ያለውን ፍቅር፣ አክብሮት፣ ውለታና ምስጋና በዝርው ጽሑፍ (ግጥም ያልሆነ፣ በወግ መልክ፣ በደብዳቤ ቅርፅ ወዘተ.) የሚገልፅበትና “ለእናቴ” የሚልበት መልካም አጋጣሚ ነው ተብሏል።
አጠቃላይ የውድድሩ ይዘት፣ የዓመቱን የእናት ባንክ ድንቅ እናት ውድድርን አስመልክቶ ተወዳዳሪዎች፣ በጽሑፍ ማቅረብ ሳያስፈልጋቸው በቃላቸው፣ በድምጽንና በምስል ቀርጸው የሚወዳደሩበትና የዓመቱ ድንቋን እናት (mother of the year) የሚያስመርጡበት ሂደት ነው፡፡
“ለእናቴ” በተሰኘው የጽሑፍ ውድድር ላይም፣ ስለእናታቸው የሚያጋሩትን ፍቅርና ስሜት ዳኞች አወዳድረው የሚያበላልጡበት ሳይሆን ይልቁንም ተወዳዳሪዎች ለእናታቸው ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት እንዴት እንደገለጹ፣ ስሜታቸውን ወደሌሎች ለማጋባት እንዴት እንደጣሩ የሚዳኙበት ዐውድ ነው ተብሏል፡፡
የማወዳደሪያ መስፈርቶቹም በተመሳሳይ መልኩ የተቃኙ ሲሆኑ የቅርፅ ጉዳዮች 50 ከመቶ፣ የይዘት ጉዳዮች 50 ከመቶ፣ በድምሩ 100 ነጥብ እንዲይዙ ተደርገው ተዘጋጅተዋል፡፡
📌 የዓመቱ ድንቅ እናት ውድድር
ይሄ ውድድር በሕይወት ያሉ እናቶች የሚመሰገኑበት የውድድር አይነት ሲሆን ከ “ለእናቴ የፅሁፍ ውድድር” የሚለይባቸው የራሱ መመዘኛዎች አሉት፤ መወዳደሪያ መስፈርቶቹም፡-
ለውድድር የሚቀርቡት ባለታሪኮች በሕይወት ያሉ እናቶች መሆን አለባቸው፤
ታሪካቸው የሚነገርላቸው እናቶች ግዴታ ወላጅ እናት (የስጋ እናት) መሆን አይጠበቅባቸውም፤ ለምሳሌ አሳዳጊ ወይም ደግሞ በሰፈር አሊያም በጎረቤት ያሉ እናቶችን ታሪክ ማቅረብ ይቻላል።
በዚህ ውድድር ላይ ስለ ሚያቀርቡት ታሪክ ከፈለጉ በጽሑፍ አሊያም በድምፅ ወይንም ደግሞ በቪዲዮ ሥራዎቻቸውን ቀርፀው ማቅረብ ይችላሉ።
➢ ውድድሩ የሚቆይበት ጊዜ ከታህሣሥ 14/2017 ዓ.ም. እስከ ጥር 14/2017 ዓ.ም. ይሆናል።
➢ መወዳደሪያ ሥራዎቻችሁን አቅራቢያችሁ በሚገኙ የእናት ባንክ ቅርንጫፎች ማስረከብ የሚቻል ሲሆን በቪዲዮና በድምፅ ቅጂ ለምታስገቡ እና ውጭ ሀገር ለምትኖሩ ደግሞ በኢሜል፤ አሊያም በእናት ባንክ ኦፊሻል የፌስቡክ ገፃችን ላይ መልዕክት ማስቀመጥ ይችላሉ።
📌 ለእናቴ የጽሑፍ ውድድር
የውድድር ጽሑፎቹ መወዳደሪያ መስፈርቶች፡-
በሌሎች የኅትመት እና የኤሌክትሮኒክስ የመገናኛ ብዙኃን ላይ ያልቀረበ ወጥ፣ አዲስና የተለየ መሆን ይኖርበታል፤
ጽሑፉ ግልጽ እና ተነባቢ እንዲሆን በኮምፒውተር ተጽፎ፣ በ12 ፎንት የፊደላት መጠን እና በ1.5 የኅዳግ መስመር መቅረብ አለበት፤
➢ በ ኤ ፎር (A4) የወረቀት ምጣኔ፣ ከሦስት /3/ ገጽ ያልበለጠ መሆን ይኖርበታል፤
➢ ለተመረጡ አሸናፊ ጽሑፎች የገንዘብ ሽልማት እና የምስክር ወረቀት ይበረከትላቸዋል፤
➢ ተወዳዳሪዎች፣ ስማቸውን እና አድራሻቸውን የጽሐፍ ሥራቸውን ባቀረቡበት ወረቀት ላይ መጻፍ የለባቸውም፤ ይልቁንም ሥራቸውን በሚያሽጉበት ፖስታ ላይ ብቻ መጻፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
እናት ባንክ አሸናፊ ጽሐፎችን በተለያዩ መንገዶች ሊጠቀምባቸው ይችላል፡፡
የማስረከቢያ ጊዜ ከዛሬ ከታኅሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥር 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ለአንድ ወር የሚቆይ ይሆናል፡፡
➢ ተወዳዳሪዎች ጽሑፋቸውን በአቅራቢያቸው በሚገኙ የእናት ባንክ ቅርንጫፎች በአካል በመገኘት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የውድድሩ መዝጊያ በተመለከተ የተወሰኑ የውድድሩ ተሳታፊዎች፣ የውድድሩ አሸናፊዎች፣ ጥሪ የሚደረግላቸው እንግዶች ባሉበት በታላቅ ድምቀት የሚደረግ ሲሆን በዕለቱም ለአሸናፊዎቹ ተወዳዳሪዎች የተዘጋጁላቸው ሽልማቶች ይበረከቱላቸዋል፡፡




