በየ ሁለት አመቱ በተባበሩት መንግስታት አዘጋጅነት የሚዘጋጀው የሮቦት እና የAI ፈጠራ ሀገር አቀፍ ውድድሩን ለመጀመር የምዝገባ ሂደቱ በዛሬው ዕለት መከናወን መጀመሩን የAI for good ፕሮጀክት ማኔጀር ሄለን አቢ ገልጸዋል፡፡
AI for good ፕሮጀክት በአርቴፍሻል ኢንተለጀንስ የታገዙ የፈጠራ ስራዎች እንዲበረታቱ እና የኢትዮጲያ ልጆች በሮቦት ፈጠራ ላይ ያላቸው ግንዛቤ እንዲዳብር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን እንዲችሉ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም ገልጻል::
ከ10 እስከ 13 በጁኒየር እንዲሁም ከ 14-18 በሲንየር ምድብ፤በተናጥል አልያም በቡድን መወዳደር የሚፈልጉ ከስምንት ባልበለጠ ቁጥር መሪያቸውን በመምረጥ መወዳደር የሚችሉበት ሁኔታ መመቻቸቱንም አስረድተዋል፡፡
ወደ 40 የሚሆኑ የአፍሪካ እና የአለም በሚሳተፉበት መድረክ ላይ ኢትዮጵያም አንደኛዋ ሆና በዘርፉ አሸናፊ ለመሆን አዲስ አበባን ጨምሮ ከክልል ከተሞች የሚመጡ ልጆችን በማሰልጠን ለውድድር ብቁ ለማድረግ መታቀዱን አብራርተዋል፡፡
ሀገር አቀፍ ውድድሩ እ.ኤ.አ ማርች 15 በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዘየም እንደሚካሄድ እና የአሸናፊዎች አሸናፊ አለም አቀፍ ውድደሩ ደግሞ ከጁላይ 8-12 ሲውዘርላንድ ጄኔቫ እንደሚካሄድም ጠቁመዋል፡፡




