ዓለምአቀፉ የፈርኒቸር፣ቤተ-ውበት እና ግንባታ አጨራረስ ኤክስፖ በፕራና ኢቨንትስ እና በአፍሪካ ትረስትድ ፓርትነርስ አዘጋጅነት በሚሊኒየም አዳራሽ ከጥር 22- ጥር 25 2017 ዓ.ም ይዘጋጃል።
የንግድ ትርኢቱ ለኢንዱስትሪው ባለድርሻ አካላት፣ ባለሞያዎች ፣ ዓለምአቀፍ አምራቾችና አቅራቢዎች እንዲሁም ገዢዎች ልዩ የንግድ ሁኔታ የሚፈጥር ሲሆን ከ 4000 በላይ ጎብኚዎች እንደሚጎበኙት ይጠበቃል ።
በኤክስፖው የፈርኒቸር አምራቾችና አስመጪዎች፣ ቤተ ውበት ላይ የሚሰሩ ተቋማት፣ የግንባታ አጨራረስ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች፣ አዲስ ቴክኖሎጂን የሚያስተዋውቁ ኩባንያዎች፣ ማሽነሪ አምራቾች፣ አገልግሎት ሰጪዎች፣ የእጅ ጥበብ ሙያ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችና፣ በዘርፉ የተሰማሩ ሁሉ የሚሳተፉበት ሲሆን የገበያ ትስስር ለመፍጠር አዳዲስ የፈርኒቸር ምርቶችን በአንድ ቦታ በቀላሉ ለማግኘት፣ የቤተ ውበት ጥበቦችን ለመመልከትና ከኢንዱስትሪው ባለድርሻ አካላትና ባለሞያዎች ጋር ለመገናኘትና ቢዝነስን ለማሳደግ ልዩ አማራጭ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
የመንግስት የግዢ ቢሮዎች፣ ከመላው ኢትዮጵያ የሚጋበዙ አርክቴክቶች፣ስራ ተቋራጮች፣ መኖሪያ ቤት፡ ህንጻ፡ ሆቴል፡ ት/ቤት ገንቢዎች፣ ሪልስቴት አልሚዎች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት በሚጎበኙት በዚህ ልዩ ኤክስፖ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።