0
#FastMereja I በአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ከቢኔ በ4ኛ ዓመት፣ 4ኛ መደበኛ ስብሰባው መወሰኑ ይታወሳል።
በውሳኔው መሠረትም ማንኛውም የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አውቶቡሶች፣ ሚዲ ባስ እና ሚኒ ባሶች ቀን ተመድበው በሚሰሩበት መስመር እና በሚከፈለው ህጋዊ ታሪፍ መሠረት እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ መመሪያ ማስተላለፉን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ይህን በሚገባ በመረዳት እስከ ምሽት 4:00 ሰዓት አገልግሎት እንዲያገኙ እና የትራንስፖርት ቁጥጥር ሠራተኞች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ለተግባራዊነቱ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ቢሮው አሳስቧል።
5 comments
Afetsatsem lay zero nachew. Higina, memeriya, demb… bemawutat 1gna. But no implementation and monitoring
አላልቅ ብለናቸው ነው አደል?
ቀንም በቅጡ በሰሩ
የነ ሌቦችዬስ ነገር?
እንኳን ምሽት ቀንም አልቻልናቸው።
ይህ ጥሩ ቢሆንም ትራፊክ ኣባላት መቆጣጠር ቢኖር ኣሪፍ ነው