banner

በአርቲስት ፍቃዱ ተክለ ማሪያም የተመሰረተው ሀበሻ የአረጋውያን መርጃ ይጣራል

ሀበሻ የአረጋውያንና ምስኪኖች መርጃ ልማት ድርጅት በአሁን ስዓት በቋሚነት 250፣በተመላላሽ 150 እና ቤት ለቤት 100 በድምሩ 500 ጧሪ፣ቀባሪ፣ ደጋፊ እና አልባሽ አጉራሽ የሌላቸውን አረጋውያን እናትና አባቶቻችንን የአልጋ ቁራኛዎችንና የአዕምሮ ህሙማንን በመያዝ ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ነገር ግን ድርጅቱ ውስጥ ቋሚ ድጋፍ እና እንክብካቤ የሚሰጥ አካል ውስን በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እና በጎ አድራጊ አካላቶች እንዲደግፋቸው በፈጣሪ እና በአረጋውያኑ ስም ሰብዓዊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ድርጅቱ ውስጥ ያሱ አረጋውያንና ምስኪኖችን በተገቢ ሁኔታ ለመደገፍ መሰረታዊ የሚባሉት ችግሮች በከተማችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ከልዩ ልዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው እና ተሰደው የሚገኙ ወንድሞችና እህቶች ብዛት መኖራቸው፣በአካባቢያችንን የተረጋጋና ዘላቂ ሰላም አለመኖሩ፣የኑሮ ውድነት፣የደጋፌዎች ቁጥር ማነስ እና ተከታታይ የሆነ ደጋፊ አካል አለመብዛቱ እና ተመሳሳይ ችግሮች መኖራቸው በድርጅቱ ውስጥ በርካታ ስር የሰደዱ ችግሮች ለመንፀባረቅ ችሏል ተብሏል።

በመሆኑም ከሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያሉብንን ችግሮች በመቀረፍ በተለይም ያጋጠሙንን ጊዚያዊና ዘለቄታዊ ችግሮች ከቻላችሁ በአካል ተገኝታችሁ እንድተጎበኙን እና አይዞን አለን እንዲትሉን በገንዘብ፣በሀሳብ፣በፀሱት/በዱዓ እንድታስቡን፣በሙያ፣በጉልበት፣በማስተባበር ከጎናችን እንድተቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

እንዲሁም የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በሰጠን 6000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ባለ 12 ወለል ዘመናዊ እና ሁሉ አቀፍ ህንፃ ግንባታ እና ከ10 አመት በኃላ ድርጅታችን ምንም ዓይነት ልመና የማያደርግ የራሱ የሆነ ገቢ ያለው ራሱን በራሱ የሚያስተዳድር የራሱ ዳቦ ቤት እና ወፍጮ ቤቶች፣የከብትና የበግ ማድለብ፣የንብ ማነብ፣የዶሮ፣የአትክልት እና ሰብል ምርቶች፣ታላላቅ የእደ ጥበብ ስራዎች፣የላርጎና ሻማ ስራ ሌሎችንም የገቢ ማስገኛ ስራዎችን በመስራት ከልመና የነፃ ድርጅት ኑ! በጋራ እናቋቁም በማለት ጥሪ ቀርቧል።

ሀበሻ የአረጋውያንና ምስኪኖች መርጃ ልማት ድርጅት በአዲስ አበባ ወሰን አቤም አካባቢ አስቴር ኃይሱ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ማስተባበረያ ቢሮ ስለከፈተ ማገዝ እና መርዳት የምትፈሰጉ በገንዘብ፣በቁሳቁስ፣በሙያ፣በማስተባበር፣ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠትና በመሳሰሉት እንድትደግፋን የይድረሱልን ሰብዓዊ ጥሪ አቅርበዋል።

ሀበሻ የአረጋውያንና ምስኪኖች መርጃ ልማት ድርጅት ለተከታታይ ስምንት ለመታት በደ/ብርሃን ከተማ ሰብዓዊ አገልግሎት እየሰጠ ያለ ድርጅት ሲሆን በስምንት አመት ግዜ ውስጥ ለ1500 ለሚሆኑ ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ፣ለዳኑት ተረጂዎች የስራ እድል በመፍጠር፣በመጦር፣ፈጣሪ በሞት የጠራቸውን ወገኖች እንደእየምነታቸው ቀብር ስነ ስርዓት በማስፈፀም፣ቤተሰቦቻቸው ጋር የማገናኘት ስራ በመስራት ለወገን ተደራሽ ለመሆን ችሏል።

ለበለጠ መረጃ
+251913023444
+251982212121
+251921132705 ይደውሉ





Leave a Comment