ጤነኛ የሆነን ታዳጊ ህመምተኛ አስመስላ በማጭበርበር ስትለምን የነበረች ግለሰብ በእስራት መቀጣቷን የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
በከተማችን በተለያዩ ጊዜያት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ሙሉ ጤነኛ ሆነው ሳለ ህመምተኛ በመምሰልና በማስመሰል ህብረተሰቡን ሲያጭበረብሩ የነበሩ ግለሰቦችና ተባባሪዎቻቸው በእስራት መቀጣታቸው ይታወቃል፤ በተመሳሳይም ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ/ም በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አካባቢ ተከሳሽ እማዋይ የተባለች ግለሰብ ወንድሜ መናገርም ሆነ መንቀሳቀስ አይችልም በማለት በዊልቸር ላይ አስተኝታ ስትለምንበት በቦታው በነበሩ የደንብ ማስከበር ባለሙያዎች ተይዛ ለፖሊስ ተላልፋ ተሰጥታለች፡፡
የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያም ተጠርጣሪዋን ተረክቦ ተገቢውን ምርመራ የማጣራት ተግባር ሲከውን ቆይቷል፡፡ ፖሊስ በምርመራ መዝገቡ ላይ የግል ተበዳይ የሰባት ዓመት ታዳጊና የተከሳሽ ወንድም ሲሆን ከትውልድ አካባቢው ወደ አዲስ አበባ ትምህርት ላስተምረው በማለት አምጥታ መለመኛ ማድረጓንም ያትታል፡፡
ፖሊስ የተከሳሿን የምርመራ መዝገብ በተገቢው የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማደራጀት ለዐቃቤ ህግ በማቅረቡ የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሿን ያርማል ሌሎችን ከመሰል ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያስተምራል ሲል በ6 ወር ቀላል እስራት እንድትቀጣ ወስኖባታል፡፡
በተለያዩ ቦታዎች ላይ መሠል የወንጀል ድርጊቶች እንደሚፈፀሙ ያስታወቀው ፖሊስ ህብረተሰቡ አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያይ እንደተለመደው ለፀጥታ አካላት በመጠቆም ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕቱን አስተላልፏል ።




10 comments
Betam chegironal leza newu😏
Biravo police tilk wongelegna yizachual
Fetri lebona yesetate
አሁን መተማመን ጠፋኮ የቱ እውነት የቱ ውሸት እንደሆነ ግራ ገባን
አልፈርድባትም እኛም በዚ ከቀጠለን መለመናችን የማይቀር ነው😔
እሺ እኛ ስራ የት ሄደን እንፈጥር☺️☺️
Deha hono temereko betkemikemet wenjalegna hono habtam mehon gid nw atfiredubat there’s no solution rather than ppl think it twice 😭😔
የሷ ጥፋት አደለም የመንግስት ጥፋት ነው ሰው ኑሮ ከብዶታል ታዲያ ምን ትብላ ኮሪደር ትብላ
ክፍ ጊዜ ነው
ችግር አይኑ ይጥፋ 👴