0
ሀያ ሶስት ህፃናት እና ሀያ ሁለት አረጋውያንን በማቀፍ የተጀመረው ዝግባ የህጻናትና አረጋውያን መርጃ የበጎ አድራጎት ድርጅት የተመሰረተበትን 16ኛ ዓመት በልዩ ልዩ መርኃግብር ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆኑን በዛሬ ዕለት በጌትፋም ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸዋል።
ድርጅቱ ከ2,650 በላይ ወላጆቻቸውን በሞት ላጡና ለከፋ ችግር የተጋለጡ ሕፃናት እና ጧሪ ያጡ አረጋዊያን እንዲሁም ችግረኛ ሴቶችን በገቢ ማስገኛ ስራ በማሰማራት የድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎት እየሰጠ ያለ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡
አሁን በዝግባ ቅጥር ግቢ ውስጥ እና በውጪ ድጋፍ የሚደረግላቸው ህፃናትና አረጋውን ቁጥር 2ሺህ 650 በላይ ሲሆን አሁን ላይ 15 የትራንስፖርት ብቻ ድጋፍ የሚደረግላቸው በጎፈቃዳኞች ሲኖሩ ለ50 ስራተኞች ቋሚ የስራ እድል ፈጥሯልም ተብሏል።




