#FastMereja I የአ/አ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን በኢንፍራቴክ የሶፍትዌር አበልፃጊ ድርጅት የተሠራ የትራንፖርት ችግሮችን የሚቀርፍና ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ፣ ጊዜንና ገንዘብን የሚቆጥብ አዲስ ሶፍትዌር ዛሬ ሐሙስ ታህሳስ 24ቀን 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል በተደረገው መርሐ ግብር ላይ ይፋ ተደረገ።
ሶፍትዌር የትራፊክ ቅጣትን እና የፖርኪንግ ክፍያን የሚያዘምን በተጨማሪም ይህ እርምጃም በሀገሪቱ ብሎም በከተማዋ የሚደረገውን ተግባርን በቴክኖሎጂ የማስደገፍ ጥረት አንድ እርምጃ ከፍ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ክበበው ሚደቅሳ ገልፀዋል።
ኢንፍራቴክ የሶፍትዌር አበልፃጊ ድርጅት በተለያዩ ተቋማት ያሉ አሰራሮችን በይበልጥ ከማዘመን ባለፈ ተቋማት ለአገልግሎት አቅራቢዎች የሚከፍሉትን የውጭ ምንዛሪ የሚያስቀር እንደሆነ ከሀገር ውስጥ ባለፈም የተለያዩ ሶፍትዌሮችን በማበልፀግ ወደ ውጪ ለመላክ መዘጋጀቱም ገልጿል ፡፡
በዘርፉ እጅግ ከፍተኛ ዕውቀትና ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተዋቀረ የቴክኖሎጂ ቡድን ያለው ሲሆን በቀጣይም ለበርካታ ወጣቶች የሥራ እድል እንደሚፈጥር የሚታመንበት ከመሆኑም በላይ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚደረገውን ጉዞ በማገዝ ረገድ ትልቁን ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል።ኤጀንሲው የትራፊክ ደንብ መተላለፍ ቅጣት አፈጻጸም ሂደትንና የፓርኪንግ አስተዳደር ሥርዓትን በቴክኖሎጂ የሚያግዝ ፕሮጄክት ተግባራዊ ሲያደርግ
*
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ኢንፍራ ቴክ ከተባለ የግል ኩባንያ ጋር በመተባበር የትራፊክ ቁጥጥርና የፓርኪንግ አስተዳደር ሥርዓት ተግባራትን ለማዘመን እና ከዚህ ጋር የተያያዙ የደንበኛ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ፕሮጄክት ቀርፆ በማጠናቀቁ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን አስታዉቆ፡፡
የትራፊክ ቁጥጥር እና የፓርኪንግ አስተዳደር መተግበሪያ ሥርዓቱ ተግባራዊ መሆኑን አስከትሎ በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢ.ፊ.ዲ.ሪ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክብር አቶ በርሆ ሃሰን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ የሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር፣ የአዲስ አበባ ኢንቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ፣ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ያብባል አዲስ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን ዋና ዳሬክተር የተከበሩ አቶ ክበበዉ ሚደቅሣ እንዲሁም ባለ ድርሻ አካላት ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ ጋዜጠኞችና፣ በዝግጅቱ የማስመረቂያ ሶፍትዌሮች ዌር ላይ የተገኙ ሲሆን ክብር ሚኒስትር ዲኤታ አስፈላጊና ትብብርና ድጋፍ እንደሚደረግና አሁን ያለዉ የትራፊት ቅጣት እንደሚያዘምን ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ እንደተናገሩት የትራፊክ ፍሰትንና ደህንነትን ለማረጋገጥ በቴክኖሎጂ የታገዘ የደንብ ማስከበር እና የፓርኪንግ አገልግሎት ሥራዎችን መሥራት ጊዜው የሚጠይቀው የቴክኖሎጂው አሠራር ነው፡፡ በከተማዋ እየታየ ያለውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስና የትራፊክ እንቅስቃሴውን ምቹ ለማድረግ በቴክኖሎጂ የተደገፉ ተግባራትን መፈጸም ለውጤታማነት ያበቃል ብለዋል፡፡
በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው ፕሮጄክት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ወደ ተግባር የሚገባ መሆኑን ጠቅሰው ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ከወዲሁ ዝግጅት እና ትብብር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡ አቶ ክበበው ለፕሮጄክቱ መሳካት አስተዋፅኦ ያደረጉ አካላትንም አመስግነዋል፡፡
ስለፕሮጄክቱ አጠቃላይ ገለፃ ያደረጉት የኢንፍራ ቴክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ቀዳማዊ ሙሉዓለም በበኩላቸው ሲስተሙ የደንብ ተላላፊዎችን ቅጣት ይመዘግባል፣ የአሽከርካሪዎችን እና የተሽከርካሪዎችን መረጃ ይመዘግባል፣ ያደራጃል፣ የፓርኪንግ ክፍያዎችን ያሰላል፣ ያሳውቃል፤ ስለዚህ ደንበኞች ክፍያውን በእጅ ስልካቸው በማንኛውም ሰዓት በየትኛውም ቦታ ላይ ሆነው መክፈል የሚችሉበትን አግባብ ተግባራዊ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ተግባራዊ የተደረገው የትራፊክ ቁጥጥር እና የፓርኪንግ አስተዳደር መተግበሪያ ሥርዓት የትራፊክ ደንብ አስከባሪዎችን እንዲሁም የተቀጪዎችን ጊዜ የሚቆጥብ፣ ቀላል፣ ቀልጣፋ እና ፈጣን አማራጭ የሚያቀርብ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በዝግጅት ላይ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣የትራፊክ ፖሊስ አካላት፣ የመገናኛ ብዙኃን ተወካዮች እና የትራንስፖርት ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን ፕሮጀክቱን ያለማው ኩባኒ እና ዋና ዳይሬክተሩ ማብራሪ እና ምላሽ በመስጠት የእለቱን ፕሮግራም ተቋጭቷል::





7 comments
Guzo besoftware?? ..Gena beletsegin
እነደዚህ አይነት አሪፍ ቀልዶችን ቶሎ ቶሎ ለህዝብ በማድረስ ሪከርድ መያዝ አለባችሁ።
Softwaru nw yemiwasdawu ways ..
አስቡት በሶፍትዌር የጃክሮስ አደባባይን ዘለን ስናልፍ 😂😂😂😂
በቃ ሜትር ታክሲ አላዋጣ ሲል ደሞ በዚህ መጣችሁ 😂😂😂
ቤንዝል ነው
Problem is not solved by software but….